ሳን ማሪኖ (ከተማ)

ከውክፔዲያ

ሳን ማሪኖ ከተማሳን ማሪኖ ዋና ከተማ ነው።

ከተማው የተመሠረተ በቅዱስ ማሪኑስ293 ዓ.ም. ነበር። ስለዚህ ክርስትና ቶሎ ከተቀበሉት አገራት አንዷ ነች። በዚያን ጊዜ እንኳን ክርስትና በሮሜ መንግሥት ገና ሕጋዊ እምነት አልነበረም። በሳን ማሪኖ በተራራማ ቦታ የሰፈሩት ክርስቲያኖች ስደተኞች ነበሩና።

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 4,493 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 43°56′ ሰሜን ኬክሮስ እና 12°26′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።