ሴይንት ህሊና ደሴት
Appearance
(ከሴይንት ሄሌና የተዛወረ)
ሴይንት ህሊና (እንግሊዝኛ፦ Saint Helena ወይም ቅድስት ሄሌና) በአትላንቲክ ውቅያኖስ የሚገኝ ደሴትና የእንግሊዝ ቅኝ (ጥገኛ) አገር ነው። ስሙ ስለ ቄሣሩ ቆስጠንጢኖስ ክርስቲያን እናት ሄሌና ተሰየመ። አሁን 4,255 ያህል ሰዎች ይኖሩበታል። ከነሐሴ 26 ቀን 2001 ዓ.ም. በፊት፣ አሰንሸን ደሴት እና ትሪስተን ደ ኩና በሴይንት ህሊና ጥገኝነት ሥር ኖረው ነበር፤ በዚያ ቀን ግን ሦስቱ ግዛቶች በሕግ እኩል ተደርገው የጠቅላላ ግዛቱ ይፋዊ ስም ከ«ሴይንት ህሊናና ጥገኞቿ» ወደ «ሴይንት ህሊና፣ አሰንሽንና ትሪስተን ደ ኩና» ተቀየረ።
ፖርቱጊዝ በ1494 ዓ.ም. ደሴቱን መጀመርያ ባገኙት ጊዜ አንድ ኗሪ አልነበረበትም። እንግሊዞች በ1651 ዓ.ም. ሰፈሩት። ሴይንት ህሊና ከአኅጉሮች ሁሉ በጣም ሩቅ ሆኖ ለረጅም ጊዜ ለግዞት አገር ይጠቀም ነበር፤ ለምሳሌ ናፖሌዎን ተማርኮ ከ1807 ዓ.ም. እስከ 1813 ዓ.ም. ድረስ ሕይወቱን እዚህ ላይ ጨረሰ።