ስሜን መንግሥት

ከውክፔዲያ

Kingdom of Semien/የቤተ እስራኤሎች ስርወ መንግስት

የሰሜን መንግስት በሚል ስያሜ የሚታወቀው፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ የአይሁድ እምነት ተከታይ ቤተ እስራኤላዊያን ፤አቋቁመውት የነበረው ስርወ መንግስት ነው። ይህ የቤተ እስራኤላዊያን ስርወ መንግስት ከ4ተኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ እስከ 17ኛው ክፍለ ዘመን የነበር መሆኑን ታሪክ ያሳያል።(323_1640)

በ4ተኛው ክፍለ ዘመን፣ኢትዮጵያ ውስጥ በአፅብሓ እና በኢዛና መሪነት የሀገሪቱ ሀይማኖት ክርስትና ሁኖ ሲታወጅ፣ በኤርትራ፣ በታሪካዊቷ ከተማ አክሱም እና አካባቢው ይኖሩ የነበሩ ቤተ እስራኤላዊያን፣ የክርስትና ሀይማኖትን ለመቀበል ፍቃደኛ ባለመሆናቸው የተነሳ፣ ከሚኖሩባቸው አከባቢዎች ለቀው እንዲሸሹ ከተደረጉ በሗላ፣ በጎንደር፣ በደምቢያ፤ በወገራ ፤በበለሳ እና ተከዜ ወንዝ ሰፍረው፣ የራሳቸውን ንጉስ ሹመው እስከ 17ኛው ክፍለ ዘመን #በ[[ህገ ኦሪነት] ለዘመናት ሲተዳደሩ ኖረዋል። ይህ የቤተ እስራኤላዊያን ስርወ መንግስት፣ እስከ 15ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ለአክሱም መንግስት ተፈታታኝ ሀይል ሁኖ ኑሯል።

  • የሰሜን መንግስት ንጉሶች:_

★ ንጉሱ ጲንሓስ~(325 _360 ዓ/ም) በኢዛና እና በአፅብሓ ዘመን

★ ከ4ተኛው ክፍለ ዘመን እስከ መጀመሪያዎቹ የ10ኛው ክፍለ ዘመን የጊድኦናዊያን ስርወ መንግስት!

ዮዲት ጊድኦን_(960 ዓ/ም _1000 ዓ/ም ) የአክሱምን ንጉሱን ድል አድርጋ ኢትዮጵያን ለ40 አመታት ያክል ለመግዛትም ችላለች።

5ተኛው ጌድኦን ~(1435_1468) በአፄ ዘረ ያእቆብ ዘመን

★ ንጉሱ ዮራም~(1528_1556) በአፄ ገላውዲዎስ ዘመን የነበር

★ ንጉሱ ራዲ~(1560_ 1563) በአፄ ሜናስ ዘመን

★ንጉሱ ካሌቭ~ አፄ ሰርፀ ድንግል ዘመን የነበር

★ ንጉሱ ዳግማዊ ጲንሀስ ~በ17ኛው ክፍለ ዘመን ነግሶ የነበረው የመጨረሻው የቤተ እስራኤላዊያን ንጉስ ።