ቤተ እስራኤል

ከውክፔዲያ
ቤተ እስራኤል ልጅ

ቤተ እስራኤልኢትዮጵያ ሲኖሩ የነበሩ የዘር ሃረጋቸው በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተገለጸው የአብርሃምያዕቆብይስሃቅ የዘር ሃረግ ሲሆን በኢትዮጵያ ለብዙ ዘመናት ሲኖሩ ቆየተው ከ1984 እ.ኤ.አ. ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ወደ እስራኤል ሃገር በመመለስ ላይ ይገኛሉ።

የመጀመሪያዎቹ ቤተ እስራኤላዊያን ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት 500 አመት በፊት፤ የመጀመሪያው የሰለሞን ቤተ መቅደስ ከፈረሰ በኋላ፣ ተሰደው ወደ ኢትዮጵያ እንደገቡ ታሪክ ያሳያል።እስከ 4ተኛው ክፍለ ዘመን ድረስ በኤርትራ እና በተለይ በአክሱም ትግራይ አካባቢዎች ኑረዋል። በ4ተኛው ክፍለ ዘመን፣ በኢትዮጵያ የሀገሪቱ ሀይማኖት ክርሥትና ሁኖ በታወጀበት ወቅት፣ የክርስትና ሀይማኖትን አንቀበልም በማለታቸው፣ በአክሱሙ ንጉስ ኢዛና ከአክሱም ተባረው በወገራ፣ ደምቢያ፣ ጭልጋ፣ ጣና ሀይቅ ዳር፣ እና በሰሜኑ ተራራማ ቦታ ከሰፈሩ በኋላ፥ በህገ ኦሪት የሚመራ የራሳቸውን ስርወ መንግስት አቋቁመው ኑረዋል። ይህ ስርወ መንግስትም የሰሜን መንግስታት (kingdom of Semien kingdom of Bete Israel) ወይም የጌድዮናዊያን ስርወ መንግስት Kingdom of Gedeon's ተብሎ ይታወቃል።ይህ የቤተ እስራኤላዊያን ስርወ መንግስት፣ ከአክሱም ስልጣኔ መንግስት እና በ13ኛው ክፍለ ዘመን ከተመሠረተው ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግስት ጋር ብዙ የጦርነት ውጣ ውረዶችን ያሳለፈ ሲሆን፣ እስከ 16ኛው ክፍለ ዘመንም ለመዝለቅ ችሏል።ይህ የቤተ እስራኤል ስረወ መንግስትም በ10ኛው ክፍለ ዘመን ድል ቀንቶት የአክሱም ስልጣኔን ካፈራረሠ በኋላ፣ በዮዲት ጌድዮን(ዮዲት ጉዲት) መሪነት ለ40 ዓመታት ያክል ጊዜ ሰፊዋን ኢትዮጵያ አስተዳድሯል ።

#የቤተ_እስራኤላዊያን ነገሥታት ሥም ዝርዝር:-

★ ንገሡ ጲንኃሥ~ (325_360 ዓ/ም)

★ ከጲንሐሥ ንግስና በሗላ (360 ዓ/ም _ 10ኛው ክፍለ ዘመን) ጊድዖናዊያን ወይም የጊድዖን ስርወ መንግስት አስተዳድሯል።ቀዳማዊ ጌድኦን፣ዳግማዊ ግድዖን፣ሳልሳዊ ግድዖን ወዘተ

★ ዮዲት ጊድዖን~(960_1000 ዓ/ም) ዮዲት ጊድዖን (ዮዲት ጉዲት) የአክሱምን መንግስት ካፈራረሰች በሗላ ኢትዮጵያን ለ40 አመት አስተዳድራለች

★ ንጉሱ ዮራም (1528_1556)

★ ንገሥ ራዲ (1560_1563)

★ ንጉሱ ካሌቭ~በአፄ ስርፀ ድንግል ዘመን የነበር እና የመጨረሻው የቤተ እስራኤላዊያን ንጉስ።

በ10ኛው ክፍለ ዘመን የነበር አንድ ኤልዳድ ሃዳኒ (Eldad Hadani) የተባለ ፃሀፊ፣ በወቅቱ ወደ አንድ ሚልዮን የሚደርስ ቤተ እሰራኤላዊ በዛሬዋ ኢትዮጵያ ይኖር እንደነበር በፅሁፎቹ አስቀምጧል።በጊዜ ሂደት አብዛኛዎቹ ፣ ክርስትናን እየተቀበሉ ቁጥራቸው እየቀነሰ በመሄዱ ዛሬ ወደ 165 ሺህ የሚሆኑ ቤተ እስራኤላዊያን በሀገረ እስራኤል ይኖራሉ።



ቤተ እስራኤል የኢትዮጵያ ብሔር ነው። አንድ ሰው ቤተእስራኤላዊ መሆን አለመሆኑን ከጥንት ጀምሮ በተዘጋጀ የዘር ሀረግ ዝርዝር(chronological order) ውስጥ ይገኛል።