Jump to content

ስብሰባ

ከውክፔዲያ

ሒሳብ ጥናት፣ ስብሰባ ማለት ከተሰጠ የነገሮች ስብስብ ውስጥ የተወሰኑትን መርጠን ሌላ ስብስብ የምንሰራበት መንገድ ማለት ነው። ይህ የስብሰባ መንገድ የተመረጡትንም ሆነ የቀሪውን ስብስብ ነገሮች ቅደም ተከተል ከግምት ውስጥ አያስገባም። ለምሳሌ፡ ሶስት ፍሬዎች ማለትም ትርንጎ፣ ብርቱካንና ሎሚ ቢኖሩ፣ አንድ ሰው በስንት አይነት መንገድ 2 ፍሬዎች ሊመርጥ ይችላል? መልሱ በ3 ዓይነት ነው፣ ይሄውም ትርንጎና ብርቱካን (1)፣ ትርንጎና ሎሚ (2) እና በስተመጨረሻ ብርቱካንና ሎሚ (3) ናቸው። ከሶስት የተለያዩ ነገሮች ሁለቱን በ3 አይነት መምረጥ ይቻላል ማለት ነው። ይሄ የሂሳብ ስብሰባ «መጀመሪያ ምን ተመረጠ፣ ቀጥሎስ ምን ተመረጠ» የሚለውን የቅደም ተከተል ጥያቄ አይመለክተም። ቅደም ተከተል አስፈላጊ ሆኖ ለሚገኝበት የምርጫ አይነት የሚጠቅመው የሂሳብ ጽንሰ ሐሳብ መፐወዝ(መደርደር) ይሰኛል።

በአጠቃላይ መልኩ አንድ ስብስብ n አባላት ቢኖሩት፣ ከዚያ ስብስብ ውስጥ የk አባላት አሰባሰብ (ያለምንም መደገጋገምና ቅደም ተከተል) ብዛት ቀመር እንዲህ ይጻፋል፡

፣ እዚህ ላይ , ሆኖም ከሆን ቀመሩ ዜሮ ይሆናል ማለት ነው።

k- ስብሰባ ያላቸው የስብስብ S አጠቃላይ ታህታይ ስብስቦች እንዲህ ይወከላሉ .

ሲነበብ « ከn ነገሮች ውስጥ ውስጥ የ k ነገሮች ስብስብ» ወይንም አቀላጥፎ ለማንበብ «ከ n ውስጥ k ሲመረጥ » ማለት ነው።

እዚህ ላይ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ከላይ ያለው የስብሰባ ቀመር የሚሰራው ስብሰባ ያለምንም ድግግሞሽ ሲካሄድ ብቻ ነው። ስብሰባው አንድን ነገር በተደጋጋሚ መምረጥን የሚፈቅድ ከሆነ ቀመሩ መስተካከል ይኖርበታል ማለት ነው። ለምሳሌ አንድ ኩባንያ ሁለት ጸሐፊዎችን መቅጠር ፈለገ። ለስራው ሁለት እጩዎች ቢቀርቡ፣ ከኒህ እጩዎች ለመምረጥ 1 አይነት መንገድ ብቻ አለ (ድግግም ካልተፈቀደ)። ድግግም ከተፈቀደ ግን በ3 አይነት ሰዎቹን መቅጠር ይቻላል፣ ማለት ሁለቱንም ስራ ለአንዱ በመስጠት (2 መንገድ)፣ ወይንም አንዱን ስራ ላንዱ ሌላኛውን ለሌላው። በሌላ ምሳሌ ለማየት፣ ከላይ የቀረቡት ሶስት ፍሬዎችን በድጋሜ መምረጥ ከተቻለ፣ 3 ተጨማሪ ጥምረቶች (ምርጫዎች) ሊኖሩ ነው ፡ እነርሱም ሁለት ብርቱካኖች፣ ሁለት ትርንጎዎች፣ እና ሁለት ሎሚዎች።

k ምርጫ ብዛት ቀመር አመጣጥ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
5 አባላት ካለው ስብስብ ውስጥ የተወሰዱ 3 አባላት ያሏቸው ታህታይ ስብስቦች

ስብስብ A ቢሰጥና የስብስብ ብዛቱ n ቢሆን , የስብስብ ብዛታቸው k ≤ n የሆኑ የስብስብ A ታህታይ ስብስቦች ብዛት የሚሰላው መጀመሪያ ከ n ውስጥ k አባላቱ በስንት አይነት መንገድ ይፐወዛሉ ተብሎ ከተጠየቀ በኋላ የሚገኘውን ውጤት በk ድርድሮች ብዛት በማካፈል ነው። ለዚህ ምክንያቱ k አባላቱ ከተመረጡ በኋላ ቢገላበጡ ምንም ለውጥ ስለማያመጡ ነው። በሒሳብ ቋንቋ ሲተረጎም፦

የቀመሩ ምሳሌዎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ለምሳሌ 6 አባላት ያሉት የእንግሊዝኛ ፊልደል ስብስብ { a, b, c, d, e, f } ቢሰጥ፣ 4 አባላት ያሏቸው ስንት ታህታይ ስብስቦች ከዚህ ስብስብ መስራት ይቻላል?

ከላይ በተሰጠው ቀመር መሰረት መልሱ እንዲህ ይሰላል፡

ሲነበብ «ከ6 ውስጥ 4 ሲመረጥ» ሲሆን ያገኘነው መልስ 15 ነው። ይህን መልስ ለማረጋገጥ ታህታይ ስብስቦቹን እንዘርዝር፦
abcd, abce, abcf, abde, abdf, abef, acde, acdf, acef, adef
bcde, bcdf, bcef, bdef
cdef

መልሱ ትክክል መሆኑን በሌላ መንገድ ማረጋገጥ ይቻላል። 4 ፊደሎች ለመምረጥ የመጀመሪያውን ፊደል ከ6 ፊደሎች መምረጥ ግድ ይላል፣ ስለዚህ የመጀመሪያው ምርጫ 6 መንገዶች አሉት። ሁለተኛውን ፊደል ለመምረጥ ቀሪ 5 ፊደሎች ስላሉ 5 መንገዶች አሉ። ሦሥተኛውን ፊደል በ4 አይነት መንገድና እንዲሁም አራተኛውን ፊደል በ 3 አይነት መንገድ መምረጥ ይቻላል። ስለሆነም 4ቱን ፊደላት በ6×5×4×3 = 360 መንገድ መምረጥ ይቻላል ማለት ነው። ሆኖም ግን ይህ የፊደሎቹን ቅደም ተከተል ግምት ውስጥ ያስገባ አመራረጥ ስልት ነው። ለምሳሌ መጀመሪያ aን መምረጥና በሁለተኛ ቦታ aን መምረጥ የግዴታ ሁለት አይነት ምርጫዎች ተደርገው ይወሰዳሉ ማለት ነው። ስለሆነም abcd እና bacd ሁለት የተለያዩ ምርጫዎች ተደርገው ተቆጥረዋል ነገር ግን በምርጫ ኅልዮት ቅደም ተከተል ግምት ውስጥ አይገባል። ስለሆነም 4 ፊደሎች አንዴ ከተመረጡ በኋላ የሚይዙት 4! የድርድር አይነት እንደ አንድ ጥምር ብቻ ነው ሚቆጠረው። ስለሆነም ከላይ የተሰጠው 360 አይነት ፕወዛ ለ4! መካፈል አለበት ማለት ነው። በሒሳብ ቋንቋ ሲተረጎም

ከሁለትዮሽ የቁጥር ስርዓት ጋር ያለው ተዛምዶ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ከላይ የተጠቀሰውን ምሳሌ በሁለትዮሽ የቁጥር ስርዓት መወከልና ማየት ይቻላል። ማለት 6 ፊደላት ተሰጥተዋል፣ 4 መምረጥ ይጠበቃል። ለምሳሌ የተመረጡት በ1 ቢወከሉ፣ ያልተመረጡት በ0 ቢወከሉ፣ እያንዳንዱ ምርጫ አራት 1'ዎችና ሁለት 0'ዎች ሊኖሩት ነው ማለት ነው። ስለሆነም ምርጫዎቹ በሞላ በውክልና ሲዘረዘሩ እንዲህ ይጻፋሉ፡

111100 111010 111001 110110 110101 110011 101110 101101 101011 100111
011110 011101 011011 010111
001111

ይህ አይነት የምርጫ እና የሁለትዮሽ ቁጥር ስርዓት ተዛምዶ ለኮምፒውተር ሳይንስ ጥናት እጅግ ጠቃሚ ነው።

ድግግሞሽ የሚፈቀድበት ምርጫ ቀመር

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ባይጄክሽን
3-አባል ባለው ብዙስብስብ (5-አባል ካለው ስብስብ የተወሰዱ) (እና)
3-አባላት ያሏቸው የ 7-አባላት ስብስብ ታህታይ ስብስቦች (በስተግራ)

n ውስጥ k ቢመረጥ እና እያንዳንዱ ተመራጭ በእያንዳንዱ ምርጫ እስከ k ጊዜ መደገም ቢችል፣ አጠቃላይ ድግግም ምርጫው ብዛት እንዲህ ይቀመራል፡

አንድ ኬክ ቤት ውስጥ 10 አይነት ኬኮች አሉ። 3ኬክ ለምግዛት ቢፈለግ በስንት አይነት መንገድ እኒህን ኬኮች መምረጥ ይቻላል?

በላይኛው ቀመር መሰረት፣ መልሱ ከ10 ውስጥ 3 ድግግም ሲመረጥ ነው ማለት ነው። በሒሳብ ቋንቋ ሲተረጎም :። 220 አይነት ምርጫዎች አሉ ማለት ነው!


የውጭ ማያያዣ(እንግሊዝኛ)

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]


12ቱ የጥምረት ቀመሮች
n ኳሶችና x ቁናዎች ቢሰጡ ኳሶቹን በቁናዎቹ ውስጥ በስንት
አይነት መንገድ ማስቀመጥ ይቻላል?
ኳሶች -n ቁናዎች-x እንደልብ ኳስ በቁና ≤1 ኳስ በቁና ≥1 ኳስ በቁና
የተሰየሙ የተሰየሙ
ያልተሰየሙ የተሰየሙ
የተሰየሙ ያልተሰየሙ
ያልተሰየሙ ያልተሰየሙ