ስቲቭ እርዊን

ከውክፔዲያ
ስቲቭ እርዊን አውስትራሊያ ውስጥ እ.አ.አ. በ2005

ስቴፈን ሮበርት እርዊን (ከፌብሩዋሪ 22፣ 1962 እ.እ.አ. እስከ ሴፕቴምበር 4፣ 2006) በአጭሩ በታዋቂነት ስሙ ስቲቭ አርዊን ይታወቃል፣ ወይም በቅፅል ስሙ አዞ አዳኙ ወይም The Crocodile Hunter ይባላል፣ ታዋቂ የቴሌቪዥን ሰው እንዲሁም የዱር አራዊት ጥናት ተመራማሪ ነበር። የአውስትራልያ ተወላጅ የሆነው አርዊን ታዋቂነቱን ያገኘው በተለይ The Crocodile Hunter በሚባለው በአለም ዙሪያ በሚታየው Wildlife Documentary ተከታታይ የቴሌቪዥን ፕሮግራሙን ከባለቤቱ ቴሪ (Terry) ጋር በመስራቱ ነበር። ሁለቱ በጋራ በመሆንም Australia Zoo የሚባል እንስሳቶች የሚኖሩበት ታዋቂ የቱሪስት መነሃሪያ ባለቤት ናቸው። አርዊን የሞተው በሴፕቴምበር 4፣ 2006 ፊልም ቀረፃ ላይ እያልለ Stingray በሚባል የባህር አሣ ደረቱ አካባቢ ከተነከሰ በኋላ ነበር።