ስጋ በል ዕፅዋት

ከውክፔዲያ
ኔፕኔዝ አተንቦሮ የተሰኘው የፊሊፒንስ ተክል ያጠመዳትን አይጥ ሲሰለቅጥ

ስጋ በል ዕፅዋት ስጋ የሚበሉ አትክልቶችን የሚወክል ስም ነው። እነዚህ አትክልቶች በትንሹም ሆነ በአብዛኛው ንጥረ ነገራቸውን የሚያገኙት ከሚበሉት ስጋ ሲሆን አቅማቸውን ግን ከመሬት ነው። አብዛኞቹ ስጋ በል ዕፅዋት በራሪ ትንኞችን በወጥመዳቸው በመክተት ገድለው ይመገቡ እንጂ አንድ አንዶቹ እስከ አይጥ እስከመያዝ ድረስ ሃይል አላቸው። ይህ እንግዳ ተፈጥሮ እነዚህ እፅዋቶች በንጥረ ነገር በትጎሳቆለ መሬት ላይ ለማደግ ያስችላቸዋል። ቻርለስ ዳርዊን ስለነዚህ ተክሎች የመጀመሪያውን ታዋቂ ጽሁፍ በ1875 አቅርቧል። [1]

ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ Darwin C (1875). Insectivorous plants. London: John Murray. http://pages.britishlibrary.net/charles.darwin3/insectivorous/insect01.htm.  "Archive copy". Archived from the original on 2006-10-23. በ2010-10-07 የተወሰደ.