ሹ-ኒኑዓ

ከውክፔዲያ

ሹ-ኒኑዓአሦር ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ ለ14 ዓመታት (ከ1590 እስከ 1576 ዓክልበ. ገደማ) የአሦር ንጉሥ ነበረ። አንዳንድ ዘመናዊ ሊቃውንት ስሙን «ኪዲን-ኒኑዓ» ብለው ያንብቡታል።

ሹ-ኒኑዓ የባዛያ ልጅ ሲባል ቀዳሚው ሉላያ «የዲቃላ ልጅ» ወይም «የማንም ልጅ ያልሆነ» ይባላል፤ ስለዚህ ሉላያ ነጣቂ ወይም እንደራሴ እንደ ነበር ይታስባል።

የሹ-ኒኑዓ ተከታይ ልጁ 2 ሻርማ-አዳድ እንደ ነበር ይላል። ከዚህ ዘመን ምንም ሥነ ቅርስ ወይም ሌላ መረጃ የለንም።

ቀዳሚው
ሉላያ
የአሦር ንጉሥ
1590-1576 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
2 ሻርማ-አዳድ