ሻርላግ
Appearance
ሻርላግ በአካድ ንጉሥ ሻርካሊሻሪ ዘመን የጉታውያን ንጉሥ ነበረ። ይህ የሚታወቀው ከሻርካሊሻሪ የዓመት ስም፣ «ሻርካሊሻሪ የጣኦታት ቤተ መቅደስ በባቢሎን ሠርቶ የጉቲዩም ንጉሥ ሻርላግን የማረከበት ዓመት» ነው። ይህ ዓመት ምናልባት 2020 ዓክልበ. አካባቢ ነበር (ኡልትራ አጭር አቆጣጠር)።
በሱመራውያን ነገሥታት ዝርዝር ደግሞ ከጉታውያን ከተዘረዘሩት ነገሥታት የ፪ኛው ስም «ዛርላጋብ» ወይም «ሳርላጋብ» ሲሆን ለ፮ ዓመታት ንጉሥነቱን እንደያዘ ይላል። በአንድ አስተሳሰብ ዘንድ ይህ ሳርላጋብ ምናልባት በሻርካሊሻሪ ዘመን የተማረከው ሻርላግ ይሆናል።