ቀለም

ከውክፔዲያ
ወጥ የቀለማት ስብጥር በተልመዶው የቀይ ቢጫ እና ሰማያዊ የቀለም ሜዳ
የሚታየው የብርሃን ህብር ቀለማት [1]
ቀለም የሞገዱ ርዝመት ድግግሞሽ ብዛት
ቀይ ~ 700–635 nm ~ 430–480 THz
ብርቱካናማ ~ 635–590 nm ~ 480–510 THz
ቢጫ ~ 590–560 nm ~ 510–540 THz
አረንጓዴ ~ 560–490 nm ~ 540–610 THz
ሰማያዊ ~ 490–450 nm ~ 610–670 THz
ወይንጠጅ ~ 450–400 nm ~ 670–750 THz
ቀለም, ርዝመተ ሞገድ, የብርሃኑ ድግግሞሽና ሃይል መጠን
ቀለም

(nm)

(1014 Hz)

(104 cm−1)

(eV)

(kJ mol−1)

አንስታይ ቀይ >1000 <3.00 <1.00 <1.24 <120
ቀይ 700 4.28 1.43 1.77 171
ብርቱካናማ 620 4.84 1.61 2.00 193
ቢጫ 580 5.17 1.72 2.14 206
አረንጓዴ 530 5.66 1.89 2.34 226
ሰማያዊ 470 6.38 2.13 2.64 254
ወይንጠጅ 420 7.14 2.38 2.95 285
ተባታይ ወይንጠጅ 300 10.0 3.33 4.15 400
በጣም ተባታይ ወይን ጠጅ <200 >15.0 >5.00 >6.20 >598

የአይናችንን የተፈተለ እንዝርት የመሰሉ ጥቃቅን ክፍሎች የብርሃን ሞገድ ሲመታቸው፣ ይህ ጉዳይ ወደ አእምሮ ተላልፎ እንደተማቹ ብርሃን የሞገድ ርዝመትና ሃይል አይምሮአችን ወደ ቀይ አረንጓዴ እና ሰማያዊ መቺውን ብርሃን ይተረጉመዋል። ማስተዋል ያለብን እዚህ ላይ ቀለም በአይንና በብርሃን የሞገድ ርዝመት ብቻ የሚወሰን ሳይሆን አእምሮም ራሱ መጠነኛ ነው የማይባል አስተዋጾ ያደርጋል። ቢጫ ቀይሰማያዊ ቀለማት በአይን ይታዩ እንጂ እነዚህን 3 ቀለማት በማዋሃድ ህልቁ መሳፍርት የሆኑ የቀለም አይኖትችን እንድናይ የሚያደርገን አእምሮአችን ነው።

የቀለም ተፈጥሮ ምንድን ነው?[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ብርሃን በራሱ የኮረንቲና ማግኔት ማዕበል ሲሆን ከዚህ ማእበል ውስጥ የሚታየው ክፍል ብቻ ብርሃን ይባላል። የማይታዩት ክፍሎች እንደነ ኤክስ ሬይየራዲዮ ሞገድአንስታይ ቀይተባታይ ወይን ጠጅን ይጠቀልላሉ። እነዚህ እንግዲህ በአይን ስለማይታዩ በተለመዶ ብርሃን አይባሉም ምንም እንኳ የብራሃን ታላቅና ታናሽ ወንድም ቢሆኑም (ማለት በተፈጥሮአቸው አንድ አይነት ነገሮች ቢሆኑም)።

ኮረንቲና ማግኔት ማዕበል የሞገድ ርዝመቱ በትንሹ 390 ቢሊዮንኛ ከሜትር እና በትልቁ 650 ብሊዮንኛ ከሜትር (በቀላል አፃፃፍ ከ390 nm እስከ 750 nm) ከሆነ በዓይን ይታያል። በነዚህ የሞግድ ርዝመት ያሉ ብርሃናት በርዝመታቸው ልክ የተለያየ ቀለማትን ይወክላሉ። ( የቀኙን ሰንጠረዥ ይመልከቱ)።

ህብረ ቀለማት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ከቀኝ የተቀመጠው ሰንጠረዥ የሚያሳየው በቀስተ ደመና ውስጥ ሊገኙ የሚችሉትን ከአንድ የጠራ የሞገድ ርዝመት ካለው ብርሃን የሚሰሩትን ቀለማት ነው። ከበታች ያለው ሰንጠረዥ የየቀለማቱን የሞገድ ርዝመትና የሞገድ ድግግሞሽ በቁጥር ያሳየናል።

መረሳት የሌለበት የቀለማት ህብር አንድ ወጥ ሲሆን በተቆራረጠ የቀለም አይነቶች የምናይበት ምክንያት ከባህልና ያስተዳደግ ዘይቤ የተነሳ ነው። ምን ማለት ነው ኢትዮጵያ ያለ ሰው ቀይ ነው ብሎ የሚያምነውን አሜሪካ ያደገ ሰው ከነጭራሹ አላስፈላጊ ቀለም አድርጎ ሊቆጥረው ይችላል። ነገር ግን ሁሉም ህብረተሰብ ብርሃንን በአንድ አይነት የቀለም ህብር እንደሚከፋፍል ተደርሶበታል። ማለት አውሮጳዊውና ኢትዮጵያዊው ቀይ ነው ብለው የሚያስቡት ነገር አንድ አይነት ነገር ነው። [2]). በሁሉም ቦታ የሚሰራባቸው የቀለም ህብር ክፍፍሎች ስድስት ሲሆኑእነሱም ቀይብርቱካንቢጫአረንጓዴሰማያዊ እና ወይን ጠጅ ናቸው። ኢሳቅ ኒውተን በሰማያዊ እና በወይን ጠጅ መካከል ያለ ኢንዲጎ የተባለ ቀለም 8ኛ የሰወች ሁሉ የጋራ ቀለም ነው ቢሎ ቢጽፍም ቅሉ አሁን እንደተደረስበት አብዛኛው ህዝብ ይህን ቀለም ለይቶ ማየት ስለማይችል ከ6ቱ የጋራ መግባቢያ ቀለማት ሊባረር ችሎአል።

የቀለም ግንዛቤ በብርሃኑ ሞገድ ርዝመት ብቻ ሳይሆን አንድ-አንድ-ጊዜ በፈጠረው ብርሃንም ሃይል ይወሰናል። ለምሳሌ በጣም ደብዛዛ ብርቱካናዊ ቢጫ እንደ ቡኒ ሆኖ እንገነዘበዋለን፣ እንዲሁ ድብዝዝ ያለ ቢጫማ አረንጓዴ በአይን ሲታይ የኦሊቭ አረንጓዴ ይመስላል።

የ ቁሶች ቀለም ከየት መጣ?[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የላይኛውና የታችኛው ክቦች በርግጥም አንድ አይነት ቀለም ነው ያላቸው, ከበዋቸውም ያሉት ወይባ አራት ማዕዘኖች አንድ አይነት ቀለም ነው ያላቸው (ይህን ካላመኑ ሌልውን ክፍል በወረቀት ጨፍነው ለክቦቹና አራት ማእዘኖቹ ቀዳዳ በመስራት ይመልከቱ); ነገር ግን በአገባብ ምክንያት እነዚህ ሁለቱ እቃወች የተለያየ ቀለማት ያላቸው ይመስላሉ

ያንድ ዕቃ ቀለም ቤእቃው ተፈጥሮ ብቻ ሳይሆን የሚወሰነው በተመልካቹም አይንና አእምሮ ጭምር እንጂ።

ግንዛቤ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የቀለም እይታ ርዕዮተ አለም ታሪክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ቀለም በአይናችን ውስጥ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ቀለም በጭንቅላታችን ውስጥ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ከተለምዶው ውጭ የሆኑ የቀለም እይታወች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ቀለም ማየት የተሳናቸው[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አራት ቀለም ማየት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ቀለምና ፊደል ደባልቆ ማየት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የትኩረት ቀለም[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የቀለም ቋሚ ምስክር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የቀለሞች ስያሜ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ከዚህ የሚክተሉት የቀለም አስተኔዎች ይህ አይነት ስያሜታ ሊይዙ ይቺላሉ። አስተኔ ማለት በስፊው ትርጉሙ ድብልቅ መጢቃ ክልስ ቅይጥ ማለት ነው። ሌላም ንግጝራዊ ዘይቤ አለው ግን አሁን ለቀለሞች መጠቀሚይ አድርገን እንውሰደው። አረጓዴ እና ፤የአርንጓዼ አስተኔ በጥቂቱ እነሆ.........ቀንበጥ -አረጓዼ የቢጫ ዘር በዉስጡ ያለው፡ ቡላ አርንጓዴ - የገረጣ አረጓዴ ፤ወይራ ፍሬ አርንጓዴ ፡ አልጌ አረንጓዴ ወይበራአርንጓዴ ወዘተ አስተኔው ድንበር የለዉም፡፡ የቢጫ- አስተኔ.......እርዴ ....ሎሚት...አደዮ.. አደይ አበባ የመሰለ....አብሺት.... አብሽ የመሰለ፡ ሰፈፌ፡ ሰፈፍ የመስለ:.....አፋር. ቢጫ ድኝቴ....ድኝ የሚመስል። የሰማያዊ አስተኔ......ክብረ ስማይ ስማያዊ ። ጉሎ ስማያዊ ፡፡ዉሃ ሰማያዊ፤ ኢንዲጎ፡ አኩዋ ማሪን ቱርኪዝ ቀይ አስተኔ .... ቀጋ ቀይ፡ አዋዝ ቀይ፡ ፍምቀይ፡ የጽጌረዳ ደም፡ ጃኖ ቀይ፡ በቾ ቀይ ፡ጥቁር ቀይ የዎይን ጠጅ አስተኔ፡ አጋሜት፡ ሸንኮሪት የቡና አይነት አስተኔ፡ መረሬ ቡና አይነት፡ ሸክሊት ቡና አይነት፡ ኡብራ ቡና አይነት፡ ዳማ ቡና አይነት፡ የሃመር አስተኔ ፡ ዎንዜ ጥሪ ሃመር፡ እንዲህ እያለ ሁልቆ -ምሳፍርት በሌለው ዝርዝር ይቀጥላል ይህ የቀለም ስያሜታ፡ ለሰአሊዎች ልዲዛይነርች ለአታሚዎች እንዲሁም ለሌሎች በጣም አስፈላጊ ነው፡፡













ማሳስብያ እትዮጵያ ዉስጥ ያሉ የባህል ቤተሰቦች ፣ስለ ቀለም የራሳቸው አምልኮ እና ፍች ነበራቸው፡ ለምሳሌ ጥንት የሸማ ጥለት እንድሁ አይለበስም ነበር፣ ጥለቱ ትርጉም እና ፍች ነበረው። ሌላው የሸዋ ኦርሞዎች ትልቅ ዛፍ ግንድ ላይ ቀይ ጨርቅ በስፊው ጠምጥመው ያስሩ ነበር። አማሮች ከቤተስቦቻቸው አንድ ሰው ስያርፍ ለሶስት ቀናት ነጭ ፈትል እንደ ማተብ ይስሩ ነበር።ይህ የጠቀስኩት ምሳሌ፣ ብቁንጽል ነው አርስቱ እጅግ ስፊ ነው ፣ ብዙ የመስክ ስራ እና ምርምር ያስፈልገዋል።


3-ኒውትራል ቀለም 4--ግራጫ አስተኔዎች 5- የቶን አስተኔው ደርጃ፣ እርከንወይም ጋማ 7-ቀለም ማጻዳት ማንጣት 8-ቀለም ማጥቆር ማጥላት 9-ህሮማቲካዊ ቀለም 10- ፕሪሜር ቀለም የቀለም ዐእማድ !!-ስብትራክቲቭ ቀለም መበጥበጥ 12-የሰአሊ መሰርታዊ ቀለም

13-የቀለም አውደ ሰንጠርዥ

14-ቀለም-አዘል ግራጫዎች-ወይም የ ሶስትዮሽ ቀለሞች 15-ኮፕሊሜንታር ቀለሞች 16-ቀዝቃዛ እና ሙቅ ቀለሞች 17- የቀለም ውሁደት ቀለ አርሞኒ 18-የቀለም ኮንትራርስት 19- ሲሙልታናዊ ኮንትራስት 20-ኮንፕሌሜንታር ቀለሞችን ማጻዳት ማንጣት 21-ኮንፕሊሜንታር ቀለሞቺን ማጥቆር 22- ኮንፕሊሜንታር ቀለሞቺን በኒውትራል ደጀን ባግራዉንድ ከላይ የተጠቀሱት የቀለም ባህሪዎች በዝርዝ እያንዳኑ ግንዛቤ ምን ማለት እንደሆነ ይተነተናል።

አን ት አልም.አይ አንት አልምት አንድምንም አቅ አይብልስ ምርት 7-ቀለም ማጻዳት ማንጣት 8-ቀለም ማጥቆር ማጥላት 9-ህሮማቲካዊ ቀለም 10- ፕሪሜር ቀለም የቀለም ዐእማድ !!-ስብትራክቲቭ ቀለም መበጥበጥ 12-የሰአሊ መሰርታዊ ቀለም

13-የቀለም አውደ ሰንጠርዥ

14-ቀለም-አዘል ግራጫዎች-ወይም የ ሶስትዮሽ ቀለሞች 15-ኮፕሊሜንታር ቀለሞች 16-ቀዝቃዛ እና ሙቅ ቀለሞች 17- የቀለም ውሁደት ቀለ አርሞኒ 18-የቀለም ኮንትራርስት 19- ሲሙልታናዊ ኮንትራስት 20-ኮንፕሌሜንታር ቀለሞችን ማጻዳት ማንጣት 21-ኮንፕሊሜንታር ቀለሞቺን ማጥቆር 22- ኮንፕሊሜንታር ቀለሞቺን በኒውትራል ደጀን ባግራዉንድ ከላይ የተጠቀሱት የቀለም ባህሪዎች በዝርዝ እያንዳኑ ግንዛቤ ምን ማለት እንደሆነ ይተነተናል።

የቀለም ረድፍ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

segera sewoch

ማጣቀሻወች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ Craig F. Bohren (2006). Fundamentals of Atmospheric Radiation: An Introduction with 400 Problems. Wiley-VCH. ISBN 3527405038. http://books.google.com/?id=1oDOWr_yueIC&pg=PA214&lpg=PA214&dq=indigo+spectra+blue+violet+date:1990-2007. 
  2. ^ Berlin, B. and Kay, P., Basic Color Terms: Their Universality and Evolution, Berkeley: University of California Press, 1969.