ቀጭኔ እና የጥርስ ሀኪሞቹ ወፎች
Appearance
ቀጭኔ በአለማችን እረጅሙ የዱር እንስሳ መሆኑ ይታወቃል፤ በዚህ እንስሳ አፍ አካባቢ ባለ ቀይ ምንቃር ኦክስፒከርስ የተሰኙ አእዋፋት ዘወትር አይጠፉም። የእነዚህ ወፎች ዋነኛ ስራቸው የቀጭኔውን ጥርስ ማፅዳት ነው። በምስራቅ አፍሪካዊቷ ታንዛኒያ የቀጭኔዎችንንና የእነዚህን ወፎች አስደናቂ ተፈጥሮአዊ መስተጋብር የሚያሳዩ ፎቶግራፎች ይፋ ተደርገዋል። በረጃጅም ዛፎች ላይ የሚገኙ ፍራፍሬዎችንና ቅጠላቅጠልን የሚመገበው ቀጭኔ በጥርሶቹ ውስጥ ሳይሰለቀጡ የሚቀሩትን ትርፍራፊ ምግብ ባለ ቀይ ምንቃሮቹ አእዋፍ ደግሞ ይመገቡታል። ቀጭኔዎቹ እና አእዋፋቱ አንዱ ያንዱን ችግር እየቀረፉ አብረው ተባብረው ይኖራሉ።