Jump to content

ቁመት መከርከም

ከውክፔዲያ
መጀመሪያ የሚታየው ሞገድ፣ የድምጽ ሞገድ ነው። ከስሩ ያለው በቁመተ ክርክም (AM) ራዲዮ ሲታዘል ሲሆን፣ ሶስተኛው በድግግመ ክርክም (FM)ራዲዮ ሲታዘል ያሳያል

ቁመት መከርከም, ወይም በ(እንግሊዝኛ) ምህጻረ ቃል AM መልዕክትን በራዲዮ ሞገድ ለመላክ የሚያገለግል በጣም ቀላሉ ዘዴ ነው። ይህ መልዕክትን የመላኪያ መንገድ ለረጀም ርቀት ግንኙነት ጠቃሚ ነው ምክንያቱም ከመሬት ከባቢ አየር ላይ በመንጠር ለብዙ ርቀት መጓዝ ይችላልና።

ቁመት እዚህ ላይ የአንድን ሞገድ ቁመት ይወክላል። ተሸካሚው ሞገድ (ራዲዮ ሞገድ) ላይ የድምፅ ሞገድ በመጫን የተሸካሚው ሞገድ ቁመት ይከረከማል። በዚህ መንገድ የተዋሃደው ሞገድ እንደማንኛውም የኤሌክትሮመግነጢስ ጨረራ በኅዋ ውስጥ ይጓዛል። በዚህ መንገድ ይተበጀው የራዲዮ መልዕክት ኤ.ኤም ራዲዮ ይሰኛል፣ የሚሰራጨውም ዝግጅት፣ በክሪስታል ራዲዮ ለመቀበል ይቻላል።

ኤ.ኤም (ቁመተ ክርክም) መልዕክቶች ብዙ ጊዜ የሚላኩት በመካከለኛናአጭር ሞገዶች ነው። በዚህ መንገድ የተላኩት ድምጾች ሊሰሙ ቢችሉም ጥራት ግን ይጎላቸዋል። ቁመተ ክርክም (ኤ.ኤም) ራዲዮ ስርጭት በኤሌክትሪክ መስመሮች እና በፀሐይ ጨረራ ሊጠለፍ ይችላል፣ አልፎ አልፎም ደመቅ-ቀዝቀዝ የማለት ባህርይ ሊያሳይ ይችላል።

በድሮ ጊዜ ቁመት ክርክም ራዲዮ የሚሰራጨው በመካከለኛ ሞገድ (ከ 540 እስክ 1600 ድግግም በሰከንድ) ነበር። አጭር ሞገድ (ከ 3000 እስክ 30,000 ኪሎ ሳይክል) ምድርን መዞር ስለሚችል፣ አንድ አንድ አገሮች የራዲዮ ዝግጅታቸውን በዚህ መስመር ሲልኩ ይታያሉ። ኤፍ.ኤም ራዲዮ ጥራቱ ከቁመተ ክርክም ራዲዮ ይሻል እንጂ፣ ብዙ ርቀት መጓዝ አይችልም።