Jump to content

ቁስ አካላዊነት

ከውክፔዲያ

ቁስ አካላዊነት ዋና የፍልስፍና ዓይነት ሲሆን፣ ዓለም የተሰራችው ከቁስ አካላት ብቻ እና ባህርይዋም የቁስ አካል አይነት ነው የሚል ነው። በዚህ አስተሳሰብ፣ ማናቸውም የመንፈሳዊም ሆነ የሐሳብ ክስተቶች ከቁስ አካላት ግንኙነት እና እነርሱን ከሚገዙ ህግጋት የሚመዘዙ ናቸው። ስለዚህም ብቸኛው የአለም ነባራዊ ክፍል፣ ከሐሳብ ነጻ ህልውና ያለው፣ ቁስ አካል ነው።

ቁስ አካላዊነትን በትይዩ የሚቃዎመው የፍልስፍና አይነት ሐሳባዊነት ይባላል።