ቂጥኝ

ከውክፔዲያ


ቂጥኝ በከፍተኛ ሁኔታ ተላላፊ በሽታ ሲሆን በዋነኛነት በግብረ ስጋ ግንኙነት ይተላለፋል። አንዳንድ ጊዜ ይህ በሽታ ለረጂም ጊዜ በመሳሳም ወይም በቅርበት የሰውነት ንክኪ ሊተላለፍ ይችላል። በተጨማሪም በቁስል ሊተላለፍ ይችላል። በቂጥኝ በሽታ የተያዘ ሰው በሽታው በውስጡ እንዳለበት ባለማወቅ ለወሲብ ጓደኛው በቀላሉ ያስተላልፋል፡፡ በእርግዝና ላይ የምትገኝ አንዲት ሴት ይህን በሽታ ወደ ህፃኑ ታስተላልፋለች፡፡ ቂጥኝ በሽንት ቤት መቀመጫዎች፣ በበር እጀታዎች፣ በመዋኛ ገንዳዎች፣ የሌላ ሰው ልብስ በመልበስና በመመገቢያ እቃዎች በፍጹም አይተላለፍም፡፡ የበሽታው መነሻ ምልክቶች ቂጥኝ ትሪፖኒማ ፓሊደም በሚባል ባክቴሪያ መነሻነት ይከሰታል፡፡ ቂጥኝ ዋና የህብረተሰብ ችግር ሲሆን ለረጂም ጊዜ የሚቆይ ከባድ የጤና ችግሮች ጥሎብን ያልፋል ከነዚህም መካከል የአእምሮ ጉዳት፣ አይነስውርነትና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ በሽታው እንዳለብን እንዴት እናውቃለን የቂጥኝ በሽታ ሶስት የህመም ደረጃዎች አሉት እነሱም 1. የመጀመሪያ ደረጃ ቂጥኝ በዚህ የህመም ደረጃ ላይ የሚገኙ በሽተኞች አንድ ወይም ከአንድ በላይ ቁስለት ይኖራቸዋል ይህ ቁስል ትንሽና ህመም አልባ ሲሆን በአፍና በብልት አካባቢ እነዚህ ቁስሎች ይከሰታሉ(ለመከሰት ከ10-90 ቀናት ይፈጅባቸዋል)፡፡ ቁስሎቹ ያለምንም ህክምና እና ጠባሳ በ6 ሳምንት ውስጥ ይድናሉ፡፡ 2. ሁለተኛ ደረጃ ቂጥኝ ይህ የህመም ደረጃ በበሽታው ከተጠቃንበት ከ6 ሳምንት እስከ 6 ወር ይጀምራል ከዚያም ለማቆም ከ1 እስከ 3 ወር ይፈጅበታል፡፡ በዚህ ደረጃ ላይ የሚገኙ በሽተኞች በእጃቸው መዳፍ እና በእግራቸው ሶል ላይ ሽፍታ ይወጣባቸዋል፡፡ በተጨማሪም እርጥባማ ክንታሮት በጭናቸው አካባቢ እንዲሁም ነጫጭ ነገሮች በአፋቸው ውስጥ ይወጣል ትኩሳትና የክብደት መቀነስ የሚጠበቁ ምልክቶች ናቸው፡፡ የተዳፈነ/የተደበቀ ቂጥኝ በዚህ ደረጃ ላይ ምንም ዓይነት የበሽታው ምልክቶች አይታዩባቸውም በሽታው የሚደበቅበት ጊዜ ነው፡፡ 3. ሶስተኛ ደረጃ ቂጥኝ ይህ የህመም ደረጃ በሽታውን ካልታከምን ወደ ከፍተኛ እና ከባድ ሁኔታ የሚተላለፍበት ነው፡፡ በልብ፣ አእምሮ፣ በነርቭ ምክንያት ፓራሊሲስ፣ አይነስውርነት፣ መስማት አለመቻል፣ ስንፈተ ወሲብ እና ሞት ሊከሰትበት የሚችልበት ደረጃ ነው፡፡ ቂጥኝ በጣም ቀላል በሆነ ዘዴ የደም ናሙና በመውሰድ ምርመራ ይደረጋል፡፡ የቂጥኝ በሽታ ህክምና በቂጥኝ በሽታ ከተጠቁ አንድ አመት ጊዜ ያልበለጣቸው ከሆነ አንድ ጊዜ የሚወሰድ ፒኒሲሊን ይህን በሽታ ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት በቂ ነው፡፡ ለፒኒሲሊን አለረጂክ የሆኑ በሽተኞች ደግሞ በቴትራሳይክሊን፣ ዶክሲሳይክሊን ወይም ሌላ ዓይነት ፀረ-ባክቴሪያ መድሃነቶች መውሰድ ይኖርብናል፡፡ የቂጥኝ ህክምና እየወሰደ ያሉ በሽተኞች ከበሽታው ሙሉ ለሙሉ እስከሚያገግሙ ከግብረ ስጋ ግንኙነት መታቀብ አለባቸው፡፡ ቂጥኝ እርጉዝ ሴቶችንና ህፃናትን እንዴት ያጠቃል እርጉዝ ሴቶች በቂጥኝ መቸ እንደተያዙ የሚወሰን ቢሆንም ለተረገዘው ህፃን የማስተላለፍ ጥሩ አጋጣሚ አላቸው፡፡ ህፃኑ ከመወለድ በፊት ማህፀን ውስጥ እያለ ይሞታል ወይም ህፃኑ ከተወለደ በኃላ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ይሞታል፡፡ የተወለደው ህፃን ምንም አይነት ምልክት አይኖረውም በህክምና እስካልተረጋገጠ ድረስ፡፡ ምልክቶቹን በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ማሳየት ይጀምራል፡፡ ያልታከሙ ህፃናት የዕድገት መዘግየት እንዲሁም ሞት ያጋጥማቸዋል፡፡ ቂጥኝን እንዴት መከላከል ይቻላል ለቂጥኝ በሽታ የመጋለጥ እድልን ለመቀነስ የሚከተሉትን ያድርጉ • በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያለንን የጠበቀ ግንኙነት መቀነስ/ማቆም • የግብረስጋ ግንኙነት አጋርዎ ሰው በቂጥኝ በሽታ መያዝና አለመያዙን የማያውቁ ከሆነ በማናኛውም የግብረስጋ ግንኙነት ወቅት ኮንዶም መጠቀም፡፡ ቂጥኝ በቀላል ምርመራና ህክምና የሚድን በሽታ ነው፡፡ ይህ ህክምና የዘገየ ቆይተን የምናደርግ ከሆነ ቋሚ የልብና አእምሮ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል ምንም እንኳን ከበሽታው ሙሉ ለሙሉ ብንድንም፡፡