ቅዱስ ቂርቆስ ወእሙ ቅድስት እያሉጣ

ከውክፔዲያ
ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ቅድስት እያሉጣ
ቅዱሳን ሰማዕታት
ቅዱሳን ሰማዕታት
ድንቅ የእናትና ልጅ እምነት
የኖሩበት ዘመን ፬ኛው ክፍለ ዘመን
የትውልድ ሀገር ሮም
የአባት ስም ቆዝሞስ
የእናትስም ቅድስት እያሉጣ
በዓለ ንግሥ ሐምሌ ፲፭ ቀን
የሚከበሩት በኢትዮጵያ ርትዕት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
በቤዛንቲያን ቤተክርስቲያን
ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን
በኮፕት ቤተክርስቲያን
በምሥራቃዊ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን
የሚታወቁት በእግዚአብሔር ኃይል በቅዱስ ገብርኤል አማካኝነት እንደ እሳት ከፈላ ውሀ ውስጥ ያለምንም ጉዳት መውጣት ።


ቅዱስ ቂርቆስ (በእንግሊዘኛ :Cyricus) (በአራማይክ : ܡܪܝ ܩܘܪܝܩܘܣ ܣܗܕܐ‎ Mar Quriaqos Sahada ፤ በተጨማሪ Quiricus Cyriacus Quiriac) ሀገሩ ሮም አንጌቤን ነው ። አባቱ ቆዝሞስ ይባላል ። እናቱ ቅድስት እያሉጣ (በእንግሊዘኛ : Julitta) (በግሪክ: ουλίττα) (በአራማይክ ܝܘܠܝܛܐ‎, : Yolitha) በትውልዷ ከአዝማደ ነገሥት ነች ። እኒህ ሁለት ሰማዕታት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና የልጇ የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ናቸው።

የሚታወቁበትም ታሪካቸው እንደሚከተለው ነው ። ዲዮቅልጥያኖስ በነገሠ በ፳ኛው ዓመት በአባ ባጋግዮስ ምክኒያት "የጣዖታት ቤቶች ሁሉ ይከፈቱ ፣ ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ይዘጉ" ብሎ በ፫፻፫ ዓ ም አወጀ ። በዚህ ጊዜ እኩሌቶቹ ተሰደዱ ቅድስት እያሉጣም ልጇ የ፫ ዓመት ሕፃን ነበረና ለርሱ ብላ ከሁለት አገልጋዮችዋ ጋር ሆና ወደ ኢቆንዮን ሸሸች ።

የዚችም ሀገር ክርስቲያኖች የባሰ ስቃይ ውስጥ ነበሩ ። መስፍነ ብሔሩ እስክንድሮስም ፣ ክርስቶስን ካጂ ለጣዖት ስገጂ አላት ። እሷም ዓይን እያለው የማያይ ጆሮ እያለው ለማይሰማ በቃልህ አዘህ በእጅህ ሠርተህ ላቆምከው ምስል አልሰግድም አለች ። አይሆንም ካልሽማ በሰይፍ ትቀጫለሽ ብሎ አስፈራራት ። እስኪ ይህንን ሕፃን ጠይቀው አለችው ። አንተ ሕፃን ወርቅ እሰጥሀለሁ ለዚህ ጣዖት ስገድ አለው ። መንፈስ ቅዱስ አድሮበታልና ፣ ራሳቸውን እንኳን ማዳን ለማይችሉ ርኩሳን ጣዖታትህ አልሰግድም አለው ። እንዲህም በመለሰለት ጊዜ ተበሳጭቶ በብረት ጋን ውሀ አፍልታቹህ ከዚያ ውስጥ ጣሏቸው አለ ታዛዦቹም በብረት ጋን ውሀ አፈሉ ድምፁም እንደ ክረምት ነጎድጉዋድ ፵፪ ምዕራፍ ድረስ ይሰማ ነበር ።

ሊከቷቸውም ሲወስዱዋቸው እያሉጣ ልቧ በፍርሀት ታወከ ቂርቆስ ግን ፍርሀቷን አርቅላት እያለ ይጸልይላት እሷንም

"ሁለተኛ ሞት አያገኘንምና እናቴ ሆይ በርቺ ጨክኚ በዚያውስ ላይ አናንያ አዛርያ ሚሳኤልን ያዳነ አምላካችን እኛንስ ያድነን የለምን"

እያለ እያጽናናት ልብሷን እየጎተተ ከእሳቱ ቀረቡ ከዚህም በኋላ እሷም ጨክና በፍፁም ልብ ሆነው ተያይዘው ከፈላው ውኃ ውስጥ ገብተዋል ።"

በዚህም ጊዜም ከዐላውያን ነገሥታት ከዐላውያን መናፍስት ቀርበው የመሰከሩለት በስሙ መከራ የተቀበሉለት ጌታ መድኃኒታች ኢየሱስ ክርስቶስ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤልን ልኮ በበትረ መስቀሉ እሳቱን አጥፍቶ የፈላውን ውኃ አቀዝቅዞ አውጥቷቸዋል ። በወጡም ጊዜ ልብሳቸው ሳይለበለብ ሰውነታቸው ሳይሸበሸብ ቢያዩ ከአሕዛብ ብዙዎቹ አምነው አንገታቸውን ለስለት ሰጥተው በሰማዕትነት ዐርፈዋል ።

እውነት ተናግረው ፃድቃን የሰማዕትነታቸውን አክሊል እንደተጎናጸፉ

ከመዝገበ ታሪክ

በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ Christianity የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።