ቅዱስ ኮላፈን

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search
የክርስቶስ ግርዛት, በፍሬድሪክ ኅርሊን

ቅዱስ ኮላፈን (በላቲን præputium ወይም prepucium), በክርስቶስ ግርዛት የተገኘ ኮላፈን ነው። በተለያዩ ግዝያት የተለያዩ በአውሮፓ ውስጥ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ተቀምጦ ይገኝ ነበር። ኮላፈኑ የተለያዩ ተአምራትን አድርጓል ተብሎ ይታመናል።

ታሪክ እና ተቀናቃኝ ጥያቄዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በአይሁዳዊያን ሕግጋት መሰረት ሁሉም ወንድ ልጆች በተወለዱ በስምንተኛ ቀናቸው ይገረዛሉ። ይህ ባህል አሁንም በተለያዩ የክርስትና አማኝ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ በጃኑዋሪ 1 ይከበራል።

ስለኮላፈኑ በመጀመሪያ የተጻፈው በArabic Infancy Gospel ሁለተኛ ምዕራፍ ውስጥ ሲሆን፣ በመጽሃፉ ውስጥም ክርስቶስ በዋሻ ውስጥ እንደተገረዘ፣ አንዲት አሮጊት ሴትዮ በወይራ ቅባት ነከራ ሳጥን በእንዳስቀመጠችው እና መድሃኒት ቀማሚ ልጇም ቅባቱን በ300 ዲናር ለማሪያም መቅደላዊት እንደሸጠው ተጽፏል። በዚህ ቅባት ደግሞ እርሷ የእየሱስ ክርስቶስ እግሮችን በፀጉሯ ማጠቧን ይገልጻል።

የክርቶስ ግርዛት, በPreobrazhenski Monastery, ቡልጋሪያ

ኮላፈኑ በመካከለኛ ዘመን ፣ አጼ ቻርላሜን ለጳጳስ ሊዮ ሶስተኛው እንደሰጡ እና ጳጳሱ ኮላፈኑን በወርቅ ሳጥን ውስጥ በChapel of St. Lawrence በተባለ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ማስቀመጣቸውን Descriptio laternansis Ecclesia ይናገራል።