ቋጠሮ ድረ ገጽ
Appearance
ቁጠሮ ድረ ገጽ ከ2001 ጀምሮ ግልጋሎት እየሰጠች የምትገኝ ድረ ገጽ ነች። ግልጋሎት መስጠት በጀመረችበት በመጀመሪያ 5 ዓመታት ውስጥ ሙሉ ትኩረቷ በአማርኛ ስነ ጽሁፍ ዙሪያ ማለትም በሥነ- ግጥም፤ ቅኔ፤ አጫጭር ልቦለዶች እና ከስነ ጽሁፍ ጋር ተያያዥነት ባላቸው የፈጠራ ስራዎች ላይ ነበር። ከ2005 ጀምሮ ግን በተለይ በምርጫው እንቅስቃሴና ከዚያ ጋር በተጎዳኙ ጉዳዮች ላይ ዘገባና ጽሁፎችን በማቅረብ ቀስ በቀስም ወደ ነጻው ሚዲያነት አድጋለች፤ ቋጠሮ ከስነ ጽሁፍ ስራዎች ወደ ዜና አውታርነት ለመለወጥ የተነሳሳችው በተለይ ከምርጫ 2005 ዋዜማ ጀምሮ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ይታይ የነበረው ለለውጥ የመነሳሳት ፍላጎት ያስደነገጠው የወያኔ መንግስት የመረጃውን ፍሰት ለመገደብ ባድረገው ከፍተኛ የአፈና እንቅስቃሴ ሳቢያ የተፈጠረውን ክፍተት ለመሸፈን በማሰብ ነው። በዚህም እንቅስቃሴዋ በአጭር ጊዜ ውስጥ በጸረ ፕሬሱ በወያኔ በመንግስት ኢላማ ውስጥ ገብታ ከ2006 ጀምሮ በኢትዮጵያ እንዳትታይ ታግዳ ቆይታለች። እንሆ ቋጠሮ ላለፉት 16 ዓመታት የድምጽ አልባው ኢትዮጵያዊ ወገን ድምጽ በመሆን የበኩሏን እየተወጣች ትገኛለች። ይሀው ጥረቷ በግፈኞች መዳፍ ውስጥ የሚገኘው መላው ኢትዮጵያዊ ነጻነቱን እስኪጎናጸፍ ድረስ ይቀጥላል።
- ቁጠሮ Archived ጁን 29, 2012 at the Wayback Machine