በመረቅ የበሰለ የዶሮ
Appearance
- 1 ዶሮ (ከ1 ኪሎ ግራም እስከ 1 ኪሎ ግራም ከሩብ የሚመዝን)
- 1 መካከለኛ ጭልፋ (100 ግራም) የተገረደፈ ባሮ ሽንኩርት
- 2 መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም) የተገረደፈ ካሮት
- 2 መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም) የተገረደፈ ቀይ ሽንኩርት
- 6 የሾርባ ማንኪያ (100 ሚሊ ሊትር) ዘይት
- 1 የሻይ ማንኪያ [[ጨው]
- 1 ዝንጣፊ ሮዝሜሪ (የጥብስ ቅጠል)
- 1 የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
- 1 ሊትር ቺክን ስቶክ (ከዶሮ የተሠራ መረቅ)
- 1. ዶሮውን መበለትና ማጽዳት
- 2. ቀይ ሽንኩርቱን በዘይት ማቁላላትና ካሮቱን እና ባሮውን ጨምሮ ማቁላላት
- 3. ቺክን ስቶኩን ጨምሮ ማንተክተክ፣ ከዚያም ሮዝሜሪውን መጨመር
- 4. የዶሮውን ሥጋ መጥበሻ ላይ በነጩ ጠብሶ በድስቱ ውስጥ ጨምሮ ማብሰል፣
- 5. ጨውና ቁንዶ በርበሬ ጨምሮ ማውጣት
- 6. ለገበታ ሲፈለግ መረቅ በሥጋው ላይ እያፈሰሱ ማቅረብ
(ከደብረወርቅ አባተ፣ ሱ ሼፍ፣ የውጭ ምግቦች አዘገጃጀት)