Jump to content

በርኒ ሳንደርስ

ከውክፔዲያ
በርኒ ሳንደርስ
የበርኒ ሳንደርስ ኦፊሲዬላዊ የሴኔት ፎቶግራፍ - እ.ኤ.አ. 2007
የበርኒ ሳንደርስ ኦፊሲዬላዊ የሴኔት ፎቶግራፍ - እ.ኤ.አ. 2007
ባለቤት ዲቦራ ሺሊንግ (ከእ.ኤ.አ. 1964 - 66)
ጄን ኦሜራ (ከእ.ኤ.አ. 1988 ጀምሮ)
ሙሉ ስም በርናርድ ሳንደርስ
የትውልድ ቦታ ብሩክሊን ኒው ዮርክ ከተማ ዩ.ኤስ.
የተወለዱት እ.ኤ.አ. ሴፕቴምበር 8 1941
ፊርማ የ{መለጠፊያ:ስም ፊርማ


በርናርድ "በርኒ" ሳንደርስ (ተወለደ በእ.ኤ.አ. ሴፕቴምበር 8 1941) አሜሪካዊ ፖለቲከኛ እና የቬርሞንት ጁኒየር ሴናተር ነው። ለእ.ኤ.አ 2016ቱ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የዴሞክራቲክ ፓርቲን በመወከል የሚወዳደር እጩ ነበር። ከእ.ኤ.አ. 2015 ጀምሮ ዴሞክራት የሆነው በርኒ ሳንደርስ ፥ በአሜሪካ ኮንግረስ ታሪክ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ያገለለ ግላዊ ፖለቲከኛ ነው። ከዴሞክራቶች ጋር ኅብረት ማድረጉ በኮሚቴ ሥራዎች ላይ ሥልጣን እንዲኖረው አድርጎ ነበር ፤ ይህም አንዳንዴ ዴሞክራቶችን አብላጫነት ሰጥቶአቸዋል። ሳንደርስ በእ.ኤ.አ. ጃኑዋሪ 2015 ላይ በሴኔት በጀት ኮሜቴ ውስጥ ራንኪንግ ማይኖሪቲ ሜምበር ሆነ ፤ ከዚያ በፊት የሴኔት የቀድሞ ወታደሮች ጉዳይ ኮሚቴ ውስጥ ሊቀ-መንበር በመሆን ለሁለት ዓመታት አገልግሏል። ራሱን ዴሞክራሲያዊ ሶሻሊስት ብሎ የሚጠራው በርኒ ሳንደርስ የሠራተኞችን መብት እና የኢኮኖሚያዊ እኩልነትን በጽኑ ይደግፋል።

ሳንደርስ ተወልዶ ያደገው ብሩክሊን ኒው ዮርክ ከተማ ውስጥ ሲሆን የተመረቀው ደግሞ በእ.ኤ.አ. 1964 ከሺካጎ ዩኒቨርስቲ ነበር።


References[ለማስተካከል | ኮድ አርም]