Jump to content

በር:ፍልስፍና/ቅርንጫፍ መግቢያዎች

ከውክፔዲያ

ፍልስፍና በተለያዩ ሰወች የተለያየ ግንዛቤና መረዳት አለው። ሆኖም ከሞላ ጎደል የፍልስፍና ዘርፎችና የሚያነሷቸው ጥያቄዎች እንዲህ ይቀርባሉ፡

  • ሥነ ዲበ አካል : እውንነት ምንድን ነው? እውን የሆነ/የሆኑ ምን ነገሮች አሉ? ከምናስተውለው ዓለም ውጭ ሌላ ዓለም አለ?
  • ሥነ ዕውቀት: አለምን መረዳት እንችላለን? እንዴት ማወቅ እንችላለን? ከራሳችን ውጭ ሌላ ሃሳብ እንዳለ እንዴት እናውቃለን?
  • ሥነ ምግባር: ሰናይዕኩይ (ጥሩና መጥፎ) ልዩነት አላቸው? ካላቸው እንዴት ልንለያቸው እንችላለን? ምን አይነት ምግባር ሰናይ (ጥሩ) ነው? ለአንድ ምግባር ዋጋ ለመስጠት የዋጋ ስርዓት መኖር አለበት፣ ይህ የዋጋ ስርዓት ከየት ይመነጫል? ከአምላክ? ወይስ ከየት? አንድ ምግባር ፍጹም ጥሩ ወይም ፍጹም መጥፎ ሊባል ይችላል? የራበው ሰው ቢሰርቅ ስርቆቱ ዕኩይ ነው? ወይንስ ሥነ ምግባር አንጻራዊ ነው? እንዴት ህይወቴን መምራት አለብኝ? ሁላችንስ እንዴት እንኑር?
  • ሥነ አምክንዮ፡ ትክክለኛ ሃሳብ እንዴት እናመነጫለን? አንድ ሃሳብ ስሜት የማይሰጥ መሆኑን እንዴት ማወቅ እችላለሁ? የክርክርን አሸናፊ እንዴት መለየት ይቻላል?
  • ሥነ ውበት፡ ኪነት ምንድን ነው? ውበት ምንድን ነው? የውበት ቋሚ መስፈርት አለው? ኪነት መስፈርቱ ነው? እንግዲያስ የውበት ትርጉሙ ምንድን ነው? የኪነት አላማ ምንድን ነው? ኪነት እኛን እንዴት ይነካናል?ኪነት ዕኩይ ሊሆን ይችላል?ኪነት የህብረተሰብን ኑሮ ይሸረሽራል ወይስ ያሻሽላል? አንድ
  • ከዋኝ የሚሰራውን ያውቃል? ለምሳሌ ድራማ ላይ ፕሬዜዳንት የሆነ ከዋኒ ዕውን ፕሬዜዳንት ሆኖ ሊሰራ ይችላል? የኪነት ተግባር የውኑን አለም መኮረጅ ነው? በመኮረጁ የቱን ያክል ነባራዊውን አለም ያጣምማል?