በሻህ ተክለማሪያም

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

በሻህ ተክለማርያም ኢትዮጵያዊ የሙዚቃ ዜማ ደራሲ እና አቀናባሪ እንዲሁም የባህልና የዘመናዊ ሙዚቃን ያደራጁ ቀዳሚ ሰው ነበሩ። ብዙ ዜማዎችን ያቀናበሩ ሲሆኑ ፣ በገናናት የሚታወቁት፣ ሙሽራዬንና ያይኔ ተስፋ የተባሉትን ዜማና ጽሁፍ ያቀረቡ ነበሩ። በኢትዮጵያ ለሚገኙ ቲያትር ቤቶችና የኪነ ጥበብ ተቋማት የተቀናበረ የሀገረሰብ ሙዚቃ የመጀመሪያው ዘር የዘሩ ነበሩ።

የህይወት ታሪክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አቶ በሻህ ተክለማርያም ከአባታቸው ከግራዝማች ተክለማርያም አጥናፈ ሰገድ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ የሺወርቅ ወልደ ጻዲቅ መጋቢት ፲፱፻፲፪ ዓ.ም. በባሌ ክፍለ ሀገር በጎባ ከተማ ተወለዱ። በ፬ ዓመት ዕድሜያቸው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት የቤተ ክህነት ትምህርታቸውን ጀምረው ሳይጨርሱ በ፰ ዓመት ዕድሜያቸው በዳግማዊ ምኒልክናተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት በመግባት ዘመናዊውን ትምህርት ገብይተዋል። በድምጸ ሸጋነታቸው የሚታወቁት በሻህ ተክለማርያም በዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት ዘመናዊ የሚዚቃ ትምህርት ሲጀመር ትምህርታቸውን በመከታተል ቫዮሊንፒያኖን መጫወት ቻሉ። ጣልያን ኢትዮጵያን ሲወር በሻህ ተክለማርያም ከፍተኛ እሥርና እንግልት ደርሶባቸው ነበር። ከወረራው በኋላም አቶ በሻህ አርቲስቶችን በመመልመል የተለያዩ የኪነ ጥበብ ትርኢቶችን ከማዘጋጀታቸውም ባሻገር ለአገራችን ኪነ ጥበብ መዳበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል። በፈረስይ ሐገር ለሙዚቃ ትምህርት ተልከው በቫዬሊን ክላሲካል ሙዚቃ ተመርቀዋል።

ማስታወቂያ ሚኒስቴር ድምጽ መቅረጫ /ቴፕ ሪኮርደር/ ባልነበረው ጊዜ የዜማና የውዝዋዜ መሪ በመሆናቸው ተጫዋቾችን ስቱዲዮ ድረስ በመውሰድ በቀጥታ ዘፈኑን ለሕዝብ እንዲተላለፍ ያደረጉ ሲሆን በኋላም ማስታወቂያ ሚኒስቴር ቴፕ ሪኮርደር ሲያመጣ ዘፈኖችን በማሰባሰብ ቀርጸው ለትውልድ እንዲቆዩ ታሪካዊ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።

ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ሽልማት 1984