Jump to content

በጀት

ከውክፔዲያ

በጀት ማለት ለወደፊቱ የሚመጣን ገቢና ወጪ የሚተነብይ የንዋይ/ገንዘብ እቅድ ነው። በዚህ እቅድ ውስጥ ቁጠባብድር እና ወጪ ይካተታሉ [1]። ግለሰቦች ወይንም ቢዝነሶች ገቢና ወጪያቸው ሲመረመር ከሞላ ጎደል ቋሚ ሆኖ ስለሚገኝ የበጀት ጥቅም ከዚህ ይመነጫል። ማለት፣ ቋሚ ገቢ ወጪ፣ ለወደፊት ይሚሆነን ለመተንበይ አመቺ ነው። ተንብዮ በበጀት መመራት ግለሰቦብ በገንዘባቸው/ንዋያቸው ላይ ሙሉ ቁጥጥር እንዲኖራቸው ያደርጋል። አላስፈላጊ ወጭወችን ለመለየት እና በአቅም መኖርን ለማወቅ ይረዳል።

የበጀት አሰራር

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ቅድሚያ መሰረት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
በጀት ምሳሌ
የወር ገቢ
የተተነበየተጨባጭልዩነት
ደመወዝ - ከስራ ፩200185-15
ደመወዝ - ከስራ ፪400410+10
ሌሎች የገቢ ምንጮች6050-10
የወሩ አጠቃላይ ገቢ660645-15
የወር ወጪ
የተተነበየተጨባጭልዩነት
ሞርጌጅ/ኪራይ3003000
መኪና ኢንሹራንስ50500
ክሬዲት ካርድ5060+10
ሴቪንግ አካውንት50500
ምግብ10090-10
የወሩ አጠቃላይ ወጪ5505500

በመጀመሪያ ደረጃ ላለፉት ሁለት ወራት የነበረን የወጪ ዓይነቶች ማወቅ ያስፈልጋል። እማይታወቅ ከሆነ ከአሁኑ በመጀመር ለሁለት ወራት መመዝገብ መልካም ልማድ ነው።

ለአንድ ወር እያንዳንዷን ወጪ ከላይ በተቀመጠው የበጀት ዓይነት መሰርት መመዝገብ ጥሩ ምክር ነው።

የወር ደሞዝን ወይንም ሌላ አይነት ገቢን ለብቻው ማስላት፣ ሁለተኛው የበጀት አሰራር ደረጃ ነው።

ከዚያ በኋላ፣ ወጪን ከገበሚ መቀነስና ውጤቱ ነጌቲቭ ከሆነ ያለ አቅም መኖርን ስለሚያመላክት ለወደፊት ይህ እንዳይሆን የወጪ ልማድን እንዴት ማስተካከል እንዳለብን ዘዴ መዘየድ።

ውጤቱ ፖዚቲቭ ሆኖ ከተገኘ ግን ያለ ገቢ ከወጪ ስለሚበልጥ ተራፊውን ገንዘብ በየወሩ ወደ ሴቪንግ አካውንት ማስተላለፍ ጥሩ ተግባር ነው።

በየወሩ በጀቱ መጻፍና መመርመር ይኖርበታል ማለት ነው። ለየጊዜው እንዲስማማ ተደርጎ መሻሻልና መታደስም ይኖርበታል። ወጭና ገቢ በሂደት በሚገባ ከታወቀ በኋላ የወደፊቱን ማቀድ ቀላል ይሆናል። ወጪን ለመቀነስ ወጭን በዝርዝር ጽፎ በዚያ ዝርዝር መሰረት መመራት ከአላስፈላጊ ወጪ ያድናል።

የበጀት ዋናው ጥቅም አንድ ግለሰብ በራሱ ገቢና ወጪ ላይ ሙሉ ቁጥጥር እንዲኖረው ማስቻሉ ነው። ስለሆነም ግለሰቦች ዕዳ ውስጥ መግባት ሲጀምሩ በቶሎ እንዲያውቁ ይሆናሉ። ስለሆነም ችግሩ ከመባባሱ በፊት አስቀድመው እርምጃ ለመውሰድ ይችላሉ።

አንድ ግለሰብ ዕዳ ውስጥ እየገባ መሆኑን መረዳት ሲጀመር መጀመሪያውኑ የዕዳውን አይነት መለየት አስፈላጊ ነው። ቅድሚያ ትኩረት አግኝተው መከፈል ያለባቸው እማይለወጡ ዕዳወች (ምሳሌ ሞርጌጅየቤት ኪራይ ..) እና ቀስ ብለው ሊከፍሉ የሚችሉ ተለዋዋጭ ዕዳዎች (ምግብ፣ የኤሌክትሪክውሃ ና ሌሎች በጥንቃቄ ሊቀነሱ የሚችሉ ቢሎች) ተለየተው ሊታወቁ ይገባል።

ዕዳዎቹ ከተለዩ በሗላ፣ ዕዳዎቹን ለማስወገድ መንገድ ማበጀት ተገቢ ነው። ለዚህ ተግባር እንዲረዳ «በደህና ጊዜ» በትንሽ በትንሹ ማጠራቀም ጥሩ ነው። ነገር ግን ይህ ተደርጎ ካልሆነ፣ ቀሪ እዳን ቀስ በቀስ ለመክፍል የሚያስችል ስምምነት ከዕዳ-ሰጪው ጋር መግባት ጥሩ ነው። ባንኮች የአንድ ግለሰብ ዕዳ ባለቤት ከሆኑ፣ ግለሰቡን ለመርዳት ፍላጎት ይኖራቸዋል፣ ምክንያቱም ከርሱ ነውና ገንዘብ የሚያገኙት። ለዚህ ተግባር እንዲረዳ ኮንሶሊዴሽን (ሁሉን ዕዳን በአንድ ላይ መሰብሰብ) እና ሪፋይናንሲንግ (ብድርን፣ በተራዘመ ጊዜ እንዲከፍሉ ማስቻል) የሚባሉ ሁለት መሳሪያወችን ባንኮች ይጠቀማሉ። እኒህን ማግኘት እዳ ከቁጥጥር ውጭ እንዳይወጣ ይረዳሉ። ሆኖም እኒህ እድሎች ካልተገኙ ዴቢት ስፔሻሊስት የተሰኙ መካሪዎችን ማነጋገር ይቻላል።

  1. Sullivan, Arthur; Steven M. Sheffrin (2003). Economics: Principles in action. Upper Saddle River, New Jersey 07458: Prentice Hall. pp. 502. ISBN 0-13-063085-3. https://www.savvas.com/index.cfm?locator=PSZu4y&PMDbSiteId=2781&PMDbSolutionId=6724&PMDbSubSolutionId=&PMDbCategoryId=815&PMDbSubCategoryId=24843&PMDbSubjectAreaId=&PMDbProgramId=23061. Archived ዲሴምበር 20, 2016 at the Wayback Machine "Archive copy". Archived from the original on 2016-12-20. በ2021-02-24 የተወሰደ.

ተጨማሪ ንባብ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]