ቢዮንሴ

ከውክፔዲያ
Beyoncé Knowles (2007)

ቢዮንሴ ጊሴሌ ኖውለስ (Beyoncé Giselle Knowles) ሙሉ ስሟ ሲሆን የአሜሪካ ዜግነት ያላት የአር አንድ ቢ (R and B) የሙዚቃ ዘርፍ አቀንቃኝ፣ የሙዚቃ አዘጋጅ፣ ተዋናይት፣ ሞዴል እና የሙዚቃ ደራሲ ናት። እ.አ.አ. በሴፕቴምበር 4 1981 ሀውስተንቴክሳስ ውስጥ ተወለደች። በልጅነቷ ጀምሮ ማቀንቀን ትወድ የነበረችው ይህች አርቲስት ገና በወጣትነት እድሜዋ ዴስትኒስ ቻይልድስ የተሰኘ የሙዚቃ ቡድን ከ ባልደረቦቿ ኬሊ ሮላንድ እና [[ዊሊያምስ ጋር በመሆን እ.አ.አ. በ 1997 ቴክሳስ ውስጥ አቋቋመች (የኋላ ኋላ ግን ቡድኑ ፈርሶ እ.አ.አ ከ2006 ጀምሮ ለብቻዋ መስራት ጀምራለች)። ቡድኑ እስከፈረሰበት አመት ድረስ በተለያዩ ስራዎች ውጠታማ ነበር። በተለይ ከባልተቤቷ ጄዚ ጋር የሰራችው ክሬዚ እን ላቭ የተሰኘው ዜማ ከፍተኛ ዝናን አትርፏል። በ2008 እ.አ.አ ያወጣችው I'm... sasha fierce አልበሟ አሁን ለደረሰችበት ከፍተኛ እውቅና ዋናውን ድርሻ ይይዛል።