Jump to content

ባህታ ገብረ ሕይወት

ከውክፔዲያ
ባህታ ገብረ ሒወት

ባህታ ገብረ ሒወትኢትዮጵያ ታዋቂ ዘፋኝ ሲሆን ብዙ ዘመናዊ የሙዚቃ ስራወችን በማቅረብ ይታወቃል።

የህይወት ታሪክ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ባህታ ገ/ሕይወት ሚያዚያ ፳፯ ቀን ፲፱፻፴፭ ዓ.ም. በትግራይ ክፍለ ሀገር አዲግራት ከተማ ተወለደ። በዚያው ከተማ የቅዳሴ ትምህርቱን አስር ዓመት ሲሞላው አጠናቋል። አባቱ በቅስናው እንዲገፋበት ቢወተውቱትም የእርሱ ምርጫ ግን እንደ አባቱ ሳልነበረ ዘመናዊው የቀለም ትምህርት እስከ ስምንተኛ ክፍል ድረስ በትግራይ ክ/ሀገር ተማረ። ከፍተኛ ትምህርቱን በመከታተል ላይ ነበር። ጎንደር ጤና ኮሌጅ ገብቶ ትምህርቱን በመተው ወደ አዲስ አበባ መጣ።

ተፈጥሮ የሰጠውን የሙዚቃ ፍቅር ገና ትንሽ ልጅ እያለ ይሞክር ስለነበር ይህንን የተረዱት አስተማሪዎቹ የአራተኛ ክፍል ተማሪ በነበረበት ወቅት እስከ ስምንተኛ ክፍል ድረስ መዝሙር እንዲያስተምር ያደርጉት ነበር። ባህታ ለሙዚቃ ይለው ፍላጎቱ እያደገ በመሄዱ ከራስ ባንድ የሙዚቃ ክፍል ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ቀርቦ ለመታወቅ በቃ።

ባህታ ከ፷ ያላነሱ ዘፈኖችን የተጫወተ ሲሆን ከነዚህም መካከል በተለይ «ደግሞ እንደምን አለሽ»፣ «ሀሎ ሀሎ»፣ «ተረሳሁኝ እንዴ» እና «ናይ ፍቅሪ ስቃይ» /ትግርኛ/ የተባሉ ዘፈኖቹ ባህታን ከሚያስተዋውቁት መካከል ዋነኞቹ ናቸው። በወቅቱ የነበረዉ የሙዚቃ ሥራ ቤተሰብ ለመመስረት የሚያስችል ገቢ የማያስገኝ ስለነበረ ባሕታም የሚወደውን የሙዚቃ ሥራ በመተው የሙዚቃው ስሜት አብሮት እያለ ኑሮውን ለማሻሻል ሲል በአዲስ አበባ ንግድ ሥራ ኮሌጅ በመግባት በሒሳብ አያያዝ ተመርቆ በዚሁ ሙያ ተሰማርቶ በመሥራት ላይ ይገኛል።

== የስራ ዝርዝር ==በግና ፍየል ማሞከት