Jump to content

ባስቴር

ከውክፔዲያ
ባስቴር

ባስቴር (Basseterre) የሴንት ኪትስ ኤንድ ኔቪስ ዋና ከተማ ነው።

የተመሠረተው በ1619 ዓ.ም. በፈረንሳዊው ሴር ፒየር በላን ደስናምቡክ ነበረ። ከዚያ የፈረንሳይ ካሪቢያን ደሴቶች ሁሉ ዋና ከተማ ሆነ። እንግሊዞች1719 ሴንት ኪትስ (ቅዱስ ክሪስቶፍ) ደሴት በማረኩ ጊዜ የደሴቱ ዋና ከተማ አደረጉት። ከተማው ብዙ ጊዜ በጦርነት፣ ቤሳት፣ በምድር መንቀጥቀጥ፣ በጎርፍ፣ በሁከትና በአውሎ ንፋስ ጠፍቷል።

አሁን የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር (1992 ዓ.ም.) 15,500 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 17°18′ ሰሜን ኬክሮስ እና 62°44′ ምዕራብ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።