ቤሊጊዩስ

ከውክፔዲያ

ቤሊጊዩስ ወይም ቤልጊዩስፈረንሣይ አፈ ታሪክ የኬልቶች (በጋሊያ፣ አሁንም ፈረንሳይ አገር) ንጉሥ ነበረ። የሉግዱስ ልጅና ተከታይ ይባላል።

እርሱ የቤልጅግ አገር (የጥንቱም «ቤልጊካ») ሞክሼ፣ እንዲሁም የኗሪዎቹ («ቤልጋያውያን» የተባለው ብሔር) አባት እንደ ነበር ተጽፏል። እንዲሁም በአሁኑ ፈረንሳይ አገር የሆኑት የቦቬባቬ ከተሞች መሥራች ተባለ።

በአንዱ መጽሐፍ ዘንድ በቤልጅግ ዙሪያ አሸናፊ ነበር። በሌላ መጽሐፍ ግን ሦስተኛው የሉግዱስ ልጅ ሆኖ ከወንድሞቹ ጋር አገሩን አካፍሎ ከሰን ወንዝማርን ወንዝ እስከ ራይን ወንዝ ያለውን ክፍላገር ለራሱ ወሰደ።

ከቤሊጊዩስ በኋላ የጣልያን ንጉሥ የዩፒተር ካምቦብላስኮን ልጅ ያሲዩስ ያኒጌና በኬልቲካ ደግሞ ንጉሥ ሆነ። ስለዚህ ዘውዱ ከሄርኩሌስ ሊቢኩስ ልጅ ጋላጤስ ትውልድ ወደ ሄርኩሌስ ሌላ ልጅ ቱስኩስ ዘር አለፈ።

ቀዳሚው
ሉግዱስ
ኬልቲካ / ጋሊያ ንጉሥ
1854-1827 ዓክልበ. ግድም (አፈታሪክ)
ተከታይ
ያሲዩስ ያኒጌና