Jump to content

ቤተ ልሔም

ከውክፔዲያ
ይህ መጣጥፍ ስለ ፍልስጥኤም ከተማ ነው። ስለ ላሊበላ ቤተ ክርስቲያን ለመረዳት፣ ቤተልሔም (ላሊበላ)ን ይዩ።
ቤተ ልሔም፣ ፍልስጥኤም

ቤተ ልሔምፍልስጤም ግዛቶችምዕራቡ ዳር (ዌስት ባንክ) የሚገኝ እጅግ ጥንታዊ ከተማ ነው። አሁንም 25,000 ሰዎች ይኖሩበታል። በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ቤተ ልሔም የኢየሱስ ልደት ቦታ ስለ ሆነ፥ በክርስትና እንደ ተቀደሰ ቦታ ይቆጠራል።

የከተማ ስም በአረብኛ بيت لحم /ቤት ላሕም/ ማለት «የሥጋ ቤት» ሲሆን፣ በዕብራይስጥ ግን ስሙ בֵּית לֶחֶם /ቤት ሌሔም/ ትርጉም «የዳቦ ቤት» ማለት ነው።