ተፈራ ካሣ
Appearance
(ከተፈራ ካሳ የተዛወረ)
ተፈራ ካሳ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ዘፋኝ የነበረ ሲሆን ብዙ ዘመናዊ የሙዚቃ ስራወችን በጊዜው በማቅረብ ይታወቃል።
ተፈራ ካሣ የዘፈን ስሜት ያደረበት ገና በልጅነቱ በበረሃ እረኛ ሆኖ ከብቶች በሚጠብቅበት ወቅት ነበር። በጓደኞቹ ዘንድ በድምፁ እየተመረጠ ለሆያሆዬ፣ ለጥምቀት፣ ለዘመን መለወጫና ለመሳሰሉት በዓላቶች አውራጅ ነበር።[1]
በ፲፱፻፵፭ ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ መጥቶ በክብር ዘበኛ ወታደርነት ተቀጠረ። ከዚያም ወደ ቲያትር ክፍሉ ተዛውሮ ድምፃዊ ለመሆን በቃ።[1]
በልጅነቱ ሲዘፍን ወላጆቹ አሰደብከን፣ ዘራችንን አበላሸኸው እያሉ ይቆጡት ነበር። ነገር ግን በሙያው እያደገ ሲመጣና ሙያው በሌሎች አገር እጅግ የሚደነቅ መሆኑንና በኢትዮጵያም እየታወቀ መሄዱን ደጋግሞ ስለነገራቸው ባሁኑ ጊዜ ስለሙያው ያላቸው አስተሳሰብ መለወጡን ገልጿል።[1]
ተፈራ እራሱ በመጣጣር የአኮርዲዮን መሣሪያ በጥሩ ችሎታ መጫወት ችሏል።[1]
ተፈራ ረቂቅ የተፈጥሮ ድምፅ ያለው፣ ረጋ ብሎ የሚያዜም፣ በብዙዎቹ ዘንድ የመወደድን ፍቅር ያተረፈ፣ አንገቱን ደፋ አድርጎ የሚታይ፣ ዝምታ ተፈጥሮው የሆነ ግሩም ድምጻዊ ነው። በዚህም ችሎታውና ተግባሩ የተነሳ ስሙ በመላው ኢትዮጵያ የታወቀ ሊሆን ችሏል።[1]
ተፈራ ካሣ ወደ ፷ የሚጠጉ ዜማዎችን እራሱ ደርሱ በዛ ያሉ ደግሞ በሰው የተደረሱለትን ተጫውቷል።[1]
- ^ ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ "ናሽናል ቢብሊዮግራፊ ቡድን፣ የአንጋፋ አርቲስቶች መዝገበ የሕይወት ታሪክ፣ መጋቢት ፳፻፣ ገጽ 25-26". Archived from the original on 2011-09-29. በ2010-12-17 የተወሰደ.