ቱኒስ

ከውክፔዲያ

ቱኒስ (تونس) የቱኒዚያ ዋና ከተማ ነው።


የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር የአካባቢውን ኗሪ ሲጨምር 1,660,300 ሆኖ ሲገመት የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ 699,700 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 36°48′ ሰሜን ኬክሮስ እና 10°11′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

ቱኒስ እጅግ ጥንታዊ እንደ ሆነ በሊብያውያንም ተሠርቶ ከክ.በ. ከ1,000 አመት አስቀድሞ ቱኔስ ተብሎ ይገኝ እንደ ነበር ይታወቃል።