ታላቅ የጫካ እሪያ

ከውክፔዲያ
?ታላቁ የጫካ እሪያ

ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ
ስፍን: ጉንደ እንስሳ (Animalia)
ክፍለስፍን: አምደስጌ (Chordata)
መደብ: አጥቢ (Mammalia)
ክፍለመደብ: ሙሉ ጣት ሸሆኔ (Artiodactyla)
አስተኔ: የአሣማ አስተኔ Suidae
ወገን: ታላቅ የጫካ እሪያ Hylochoerus
ዝርያ: 'H. meinertzhageni
ክሌስም ስያሜ
Hylochoerus meinertzhageni

ታላቅ የጫካ እሪያአፍሪካ ጫካዎች የሚገኝ የእሪያ ዘመድ ነው። በጥቂት መጠን በኢትዮጵያም ተገኝተዋል። ለወገኑ Hylochoerus ብቸኛው ዝርያ ነው።

ታላቅ የጫካ እሪያ ብዙ ረጅም ብርቱካን እና ጥቁር ጸጉር አለው። የረዘመ ክራንቻ ጥርስ አለው። በተለይ እጽ ይበላል፣ አንዳንዴም ጥምብ ያንሳል። በብዙ ቦታዎች በተለይ በሌሊት ይሂዳል፣ ሆኖም በቅዝቃዛ ወቅት ወይም ከሰዎች ሲራቅ በቀን ሊታይ ይችላል። እስከ ሀያ በአንድ መንጋ አብረው ይሄዳሉ።

ታላቁ የጫካ እሪያ ገና ለመዳ አልተደረገም፣ በቀላሉ ለመዳ እንደሚደረግ ነበር ይታስባል። በጫካ ውስጥ ወንዱ ግፈኛ ሊሆን ይችላል፣ ወይም እርስ በርስ ሊታገሉ ወይም ቡራቡሬ ጅብን ከጥምብ ሊያባረሩ ይችላሉ። በግስላ ወይም በብዙ ቡራቡሬ ጅቦች ሊነጠቅ ይቻላል።