ሥርአተ ምደባ
Appearance
(ከሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ የተዛወረ)
ሥርአተ ምደባ (ታክሶኖሚ) በሥነ ሕይወት ሕያዋን ነገሮች በሚጋሯቸው የጋራ ባህሪያት ላይ በመመስረት ስያሜ የመስጠት፣ ባህሪያቸውን የመተንተን እና በተለያዩ ቡድኖች ምደባ የመስጠት ሳይንሳዊ ጥናት ነው፡፡
ሕያዋን ነገሮች በእርከኖዎች ይመደባሉ፤ እነዚህ እርከኖዎች ምደባዊ ደረጃ ይሰጣቸዋል፤ በተወሰነ ደረጃ ላይ የሚገኙ እርከኖዎች ተሰብስበው አንድ ከፍ ያለ ደረጃ ያለው የበለጠ አካታች የሆነ እርከኖ ይፈጥራሉ፡፡ በዚህ መልኩ ምደባዊ ደረጃ ይፈጠራል፡፡
ስዊድናዊው ቦታኒስት ካርል ሊኔውስ ህይወት ያላቸውን ነገሮች በክሌሰም ስያሜ ለመሰየም እና ለመፈረጅ ሊኔአን ታክሶኖሚ የተሰኘ ደረጃዊ ስርአት አዘጋጅቶ ስለነበር ለዘመናዊው ስርዓተምደባ እንደ አባት ይቆጠራል፡፡
በዘመናዊው አጠቃቀም ዋናዎቹ የእርከኖ ደረጃዎች የሚከተሉት ናቸው፡-
በዘልማድ እነዚህ ደረጆች የሮማይስጥ ስያሜ አላቸው፤ ለምሳሌ የሰው ልጅ homo sapiens /ሆሞ ሳፒየንዝ/ «ጥበበኛ ሰው» ይባላል።