እንስሳ

ከውክፔዲያ

እንስሳ የሕያው ነገር አይነት ሆኖ የሚያድገው ከብርሃን አማካይነት እንደ አትክልት ሳይሆን ከመብላት ነው።

ስነ ሕይወታዊ ክፍፍሎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሥነ ሕይወት ጥናት ዘንድ፣ እንስሳ አንድ የሕይወት ስፍን ሲሆን 34 ክፍለስፍኖች በውስጡ ይመደባሉ። ከነዚህም መካከል፣ ብዙዎቹ ጥቃቅን ትሎች ወይም ትል መሳይ አይነቶች ናቸው።

  1. ሰፍነግ Porifera 7700 ዝርዮች (የባሕር እንስሳ)
  2. ዝርግ ቀዲም Placozoa 1 ዝርያ (የባሕር ደቂቅ ዘአካል)
  3. ሚዶ ማርመላታ Ctenophora 150 ዝርዮች (የባሕር እንስሳ)
  4. የዛጎል ድንጋይ ክፍለስፍን Cnidaria 11,000 ዝርዮች (የባሕር እንስሶች፣ ማርመላታ ዓሳ ያጠቅልላል)
  5. ሆድ የለሽ Xenacoelomorpha 100 ዝርዮች (የባሕር ደቂቅ ዘአካል)
  6. ቀጥታ ዋናተኛ Orthonectida 26 ዝርዮች (የባሕር ደቂቅ ዘአካል፤ የዛጎል ለበስ፣ የሾህ ለበስ ወይም የትል ተውሳክ ነው)
  7. ጥፍጥፍ ትል Platyhelminthes 25,000 ዝርዮች (የውሃ ወይም የተውሳክ ትል እንደ ኮሶ)
  8. ሽፋሽፍታም ትል Gastrotricha 690 ዝርዮች (የባሕር ደቂቅ ዘአካል)
  9. ሽክርክር እንስሳ Rotifera 2000 (የባሕር ደቂቅ ዘአካል)
  10. እሾህ-ራስ ትል Acanthocephala 1100 (ደቂቅ ዘአካል፣ በተለይ የሸርጣንና የሸርጣን-በል ዳክዬ ሆድ ተውሳክ)
  11. መንጋጭላ ትል Gnathostomulida 100 (የባሕር ደቂቅ ዘአካል)
  12. ጥቃቅን መንጋጭላ ትል Micrognathozoa 1 (በግሪንላንድ የተገኘ ደቂቅ ዘአካል)
  13. ፍላጻ ትል Chaetognatha 100 (ትንሽ የባሕር ትል)
  14. የጐርምጥ ተውሳክ Cycliophora 3 (በጐርምጥ አፍ ዙሪያ ተቀምጦ ትርፍ ምግቡን የሚበላ)
  15. ባለአንጓ ትሎች Annelida 17,000 (የባሕርና የምድር፣ አልቅት ያጠቅልላል)
  16. የስምንት-እግር ኩላሊት ተውሳክ Rhombozoa 100 (በስምንት-እግር ኩላሊት ውስጥ የሚገኝ)
  17. ጥብጣብ ትል Nemertea 1200 (የባሕር ትል)
  18. ኮቴ ትል Phoronida 11 (ትንሽ የባሕር እንስሳ)
  19. የፋኖስ ዛጎል Brachiopoda 300-500 (ትንሽ የባሕር እንስሳ)
  20. ዛጎል ለበስ Mollusca 112,000 (ባሕርና ምድር፤ ቀንድ አውጣስምንት-እግርኦይስተር ወዘት.)
  21. ኦቾሎኒ ትል Sipuncula 144-320 (የባሕር ትል)
  22. ዋንጫ ትል Entoprocta 150 (የባሕር ደቂቅ ዘአካል)
  23. ሳርንስት እንስሳ Bryozoa 5000 (የባሕር ደቂቅ ዘአካል)
  24. የጭቃ ደራጎን Kinorhyncha 150 (የባሕር ወለል ደቂቅ ዘአካል)
  25. ጥርግ ራስ Loricifera 122 (የባሕር ወለል ደቂቅ ዘአካል)
  26. ቁላ ትል Priapulida 20 (የባሕር ትል)
  27. ጭራ ትል Nematomorpha 320 (የውሃ ትል፣ እጭ የጋጥመ-ብዙ ተውሳክ ነው)
  28. ድቡልቡል ትል Nematoda 25,000-1,000,000 (የትም ቦታ የሚገኝ ጥቃቅን ትል ወይም ወስፋት)
  29. ወላንሳ ትል Onychophora 200 (ትንሽ የምድር ትል፣ በገሞጂዎች የሚገኝ)
  30. የውሃ ድብ Tardigrada 1000 (ደቂቅ ዘአካል፣ በውሃ ሁሉ የሚገኝ)
  31. ጋጥመ-ብዙ Arthropoda 1,200,000 (ሦስት አጽቄሸረሪትአምሳ እግርሺ እግርሸርጣንጐርምጥ ወዘተ.)
  32. ሾህ ለበስ Echinodermata 7000 (የባሕር እንስሶች፣ ኮከብ አሳ ወዘተ.)
  33. የበሉጥ ዘር ትል Hemichordata 100 (የባሕር ትል)
  34. አምደስጌ Chordata 100,000 (ባለ አከርካሪ ሁሉ - አሳአምፊናልተሳቢ እንስሳአዕዋፍጡት አጥቢ)