Jump to content
አማርኛ ውክፔድያን አሁኑኑ ማዘጋጀት ትችላላችሁ - ተሳተፉበት!

ቀንድ አውጣ

ከውክፔዲያ
ተራ የአጸድ ቀንድ አውጣ የንፍጥ ጎዳና ሲተው

ቀንድ አውጣዛጎል ለበስ እንስሳ መደብ ነው። የየብስ ቀንድ አውጣ ብቻ ሳይሆኑ ብዙ የባሕር ቀንድ አውጣ ወይም የሐይቅ ቀንድ አውጣ ዝርዮች ደግሞ አሉ። በዚህ መደብ ያሉት አንዳንድ ዛጎልን አይለብሱም፣ ዛጎል-የለሽ ዝርዮችም ስለግ (ከእንግሊዝኛው) ተብለዋል።

የቀንዳውጣ «ቀንድ» በውነት ቀንድ ሳይሆን ዓይኖቹ ያሉበት መዳህሰስ ነው።

  • ቀንድ አውጣ ሰብልን ስለሚበላ አስቸጋሪ ነው።
  • ብዙ ቀንድ አውጣ የበሽታ ተሽካሚዎች ሲሆኑ ለጤንነት አስቸጋሪ ነው።
  • በአንዳንድ አገራት አበሳሰል ውስጥ፣ ቀንድ አውጣ እንደ ምግብ ይበላል።
  • የቀንድ አውጣ ዛጎል ለጌጣጌጥና እንደ እንቁ ክብርን አገኝቷል።

ግብርና ቀንዳውጣ ለመከልከል፣ መዳብ ይሠራል፤ ቀንዳውጣዎች መዳብን አይወዱምና። የመዳብ ቀለበት በዛፍ ግንድ ዙሪያ ቢቀመጥ ቀንዳውጣ እስከ ፍሬው ድረስ አይደርስም። ቡናአጸድ ቀንድ አውጣ በጣም መርዛም ሲሆን የተፈጨ ቡና ዱቄት ቢሆንም በማዳበሪያው መጨምሩ ይከለክላቸዋል።

በኢትዮጵያ የተገኙት ተክሎች እንዶድ እና ጓሳ በተለይ በሽታ-አዘልን ቀንዳውጣዎች ለመግደል አገልግለዋል፣ ይህም በምዕራብ ሳይንስ ታውቋል።

ቀንዳውጣ በነዚህ አገራት አበሳሰል ውስጥ እንደ ምግብ ይበላል፦ ፖርቱጋልእስፓንያፈረንሳይቤልጅግጣልያንቡልጋሪያግሪክማልታቆጵሮስሞሮኮአልጄሪያጋናናይጄሪያካሜሩንላዎስካምቦዲያቬትናምፊልፒንስኢንዶኔዥያኔፓልቻይና

የአጸድ ቀንድ አውጣ (Cornu aspersum) የሚመንጨው ንፋጭ እዠት ለሰዎች ቆዳ ቁስልን ለማሳደስ እንዳቀለለ ይታወቃል፤ ስለዚህ ይህ እዠት በአንዳንድ የቆዳ ክሬም ውስጥ ተጨምሯል።

በቀንድ አውጣ መደብ፣ አንዳንድ ዝርዮች እንደ ሌሎች እንስሳት ሁሉ በወንድና በሴት ጾታዎች ይከፈላሉ። አብዛኞቹ የቀንድ አውጣ ዝርዮች ግን አንድ ጾታ ብቻ አላቸው እሱም ፍናፍንት ነው። እያንዳንዱ ፍናፍንት ቀንዳውጣ ዘሩንም እንቁላሉንም ይፈጥራል ማለት ነው። በወሲብ ጊዜ ሁለቱ ፍናፍንት ቀንዳውጦች መጀመርያ እርስ በርስ «የፍቅር ጦር» ይጥላሉ፤ ይህ እንደ ስለታም አጥንት የሚጣል ፍላጻ የሌላውን ቀንዳውጣ ይወጋል። ከዚህ በኋላ ዘርን በመለዋወጥ እርስ በርስ እርጉዝ ያደርጋሉ። አንዳንዴም አንድያ ፍናፍንት ቀንዳውጣ ለብቻው እራሱን እርጉዝ ለማድረግ ይቻላል። እርጉዝ ከሆኑ ብዙ መቶ ትንንሽ እንቁላሎች ይጥላሉ።

የቀንዳውጣ እግር በንፋጭ ምንጨት ስለሚሸፈን ቀስ ብሎ ሲሄድ ሲሄድ የንፋጭ ጎዳና ይተዋል። ከትንሽ በኋላም ሲደርቅ ይጠፋል። ይህ በመዝሙረ ዳዊት 58:8 (በእብራይስጥ) ይጠቀሳል፤ «(ኀጥኣን) እንደሚቀልጥ ቀንድ አውጣ ያልቃሉ»፣ በዘመናዊው አማርኛ ትርጉም ግን «ቀንድ አውጣ» ሳይጠቅስ «እንደሚቀልጥ ሰም ያልቃሉ» አለ።