እንዶድ

ከውክፔዲያ

እንዶድ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።

የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አስተዳደግ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በመላው ኢትዮጵያ ግዛት በተለይም በወይና ደጋ ተራ ነው።

በአፍሪካና በማዳጋስካር፣ በተለይም በኢትዮጵያና ኤርትራ ይገኛል።

የተክሉ ጥቅም[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሥሩ ወይም ቅጠሉ ተደቅቆ በውሃ ለቁርባ ወይም ወፍ በሽታ ይጠጣል። የሥሩ መረቅ ለጨብጡ ያከማል። በአነስተኛ መጠን ካልሆነ ሊገድል ይችላል።[1] የወንድ እንዶድ ሥር ተድቅቆ በውሃ ደግሞ ውሻ በሽታን ለማከም ይጠጣል።[2] ወይም እንዲህ በጤፍ ቂጣ ይበላል።[3]

የእንዶድ ቅጠል ጭማቂ ለእከክ መቀባቱ፣ ወይም ለሆድ ትል መጠጣቱ ተዝግቧል።[4] የፍሬውም ለጥፍ ለቁስል ይለጠፋል።

ፍሬው ተደርቆ ተድቅቆ ለሳሙና መጠቀሙ ጥንታዊ ልማድ ነው። ደግሞ አሣን በማደንዘዝ በአጥማጆች ተጠቅሟል።

በ1956 ዓም፣ አንድ የኢትዮጵያ ሳይንቲስት ዶ/ር አክሊሉ ለማ የእንዶድ ሳሙና ዛጎል ለበስን እንደሚያጥፋ ለይተው አገኙ። የቢልሃርዝያ በሽታ በዛጎል ለበስ ስለሚፈጠር፣ ቢልሃርዝያን በመከላከል ከፍ ያለ ሚና አገኝቷል። ዶክተሩም የእንዶድ ማዕከል ኣቋቁመዋል በዚህም ዕውቅናን እትርፋል። ሌሎችንም አስቸጋሪ ቀንድ አውጦች ወይም ተባዮች ለማጥፋት ስለሚችል እንዶድ በስሜን አሜሪካ ትኩረትና ፓቴንቶች አገኝቷል።


  1. ^ አማረ ጌታሁን - SOME COMMON MEDICINAL AND POISONOUS PLANTS USED IN ETHIOPIAN FOLK MEDICINE Archived ጁላይ 31, 2017 at the Wayback Machine March 1976 እ.ኤ.አ.
  2. ^ በደብረ ሊባኖስ ዙሪያ ያለው ሕዝብ መድሃኒታዊ እጾች እውቀናና ጥቅም 1998 ዓም ከጥላሁን ተክለሃይማኖት፣ ሚሩጸ ጊዳይ፣ ግርማይ መድኅን፣ ያለም መኮነን፣ አዲስ አበባ ዩኒቬርሲቴ፣ አክሊሉ ለማ ተቋም
  3. ^ የዘጌ ልሳነ ምድር ባህላዊ መድሃኒት ጥናት 1999 ዓም ከጥላሁን ተክለሃይማኖት፣ ሚሩጸ ጊዳይ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
  4. ^ የፍቼ፣ ኦሮሚያ ባህላዊ መድሃኒት ጥናት 2006 ዓም ከዓቢዩ እኒየው እና ሌሎች፣ ጎንደርና አዲስ አበባ ኡኒቨርሲቲዎች ሥነ ፍጥረት ኮሌጆች