አክሊሉ ለማ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ዶ/ር ኣክሊሉ ለማኢትዮጵያ ሃኪም ነበሩ።

ቢልሃርዝያ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሺስቶሶሚያሲስ ወይም ቢልሃርዝያ (Bilharziasis) ሺስቶሶማ በሚባሉ የደም ወስፋቶች ደም ውስጥ መገኘት የሚመጣ የሰው በሽታ ነው። ወንድና ሴት ትሎች ተገናኝነው በመጣበቅ የሰው ደም ውስጥ በመኖር ብዙ ሺህ እንቁላሎች ያፈራሉ። እንቁላሎቻቸው ከሽንት ጋር ሲወጡም ደም ሊያሸኑ ይችላሉ። እንቅላሎቹ ከሰገራና ከሽንት ጋር ከሰውነት ወደ ውጪ ከወጡ በኋላ ተፈልፍለው ሚራሲዲያ የሚባሉት የትሉ ኣንድ ዓይነት ደረጃ ቀንድ ኣውጣ ውስጥ ገብተው ይራባሉ። ከእዚያም ከቀንድ ኣውጣው ወጥተው ውሃ ውስጥ በመቆየት የሰውን ቆዳ በስተው ወደ ደም ስር ይገባሉ። በሽታው ሰውን የሚይዘው ሰርኬርያ የሚባሉት የትሉ ኣንድ ዓይነት ደረጃ ሰው ሲዋኝ ወይም በባዶ እግሩ ውሃው ውስጥ ሲሄድ ቆዳን በመብሳት ወደ ሰውነት ስለሚገቡ ነው።

ዶ/ር ኣክሊሉ ለማ እንዶድ ቀንድ ኣውጣዎችን መግደል ስለሚችል በሽታውን ለመቆጣጠር እንደሚራዳ ስለደረሱበት ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል። ዶ/ር ኣክሊሉ ስለ እንዶድ ጥቅምና የውሃ ትላትል መግደል ችሎታ በማግኘታቸው በ፲፱፻፷፮ ዓ.ም. እና በ፲፱፻፹፮ ዓ.ም. ከባልደረቦቻቸው ጋር የዩናይትድ እስቴትስ የፈጠራ ባለቤትነት ወይም ፓተንቶች ኣግኝተዋል። የእንዶድ ማዕከልም ኣቋቁመዋል። ስለ እንዶድ ምርምር ለብዙ ዓመታት በኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ ስላደረጉት ኣስተዋጽዖ “ራይት ላይቭሊሁድ ኣዋርድ” ወይም “Right Livelihood Award” የሚባል ሽልማት በ፲፱፻፹፩ ዓ.ም. ተሰጥቷቸዋል። እንዲሁም ስለ እንዶድ ምርምር ለብዙ ዓመታት ከዶ/ር ኣክሊሉ ጋር ስላደረጉት ኣስተዋጽዖ ዶ/ር ለገሠ ወልደዮሓንስ “ራይት ላይቭሊሁድ ኣዋርድ” የሚባል ዕውቅና በ፲፱፻፹፩ ዓ.ም. ተሰጥቷቸዋል።a

የውጭ መያያዣዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]