Jump to content

ግብረ ስጋ ግንኙነት

ከውክፔዲያ
(ከወሲብ የተዛወረ)

ግብረ ስጋ ግንኙነት ወይም ሩካቤ ስጋ ማለት በሴትና በወንድ መካከል ለስሜት እርካታ የሚደረግ ግንኙነት ወይም ፍቅር መሥራት ነው። ይህም ለመባዛት ወይም ለመዋለድ አስፈላጊ ከመሆኑ በላይ የወሲብን እርካታዊ ፍላጎት ለማሟላት ሊሆን ይችላል።

ሥነ ሕይወት ዘርፍ ሲታይ ወሲብ፣ የእንስትን (ሴትን) እና የተባእትን (ወንድን) ዘር በማዋሃድ ወይንም በማዳቀል፣ የፍጡራን ዝርያ (species)፣ ከአሮጌ ወደ አዲስ እየታደስ፡ በቅጥልጣይ ረገድ ለረዥም ጊዜ እንዲቆይ የሚያስችል፣ ተፈጥሮ የቸረችው ተፈጥሯዊ ተግባር ነው። በእያንዳንዱ የፍጡር ዝርያ ተባእትና እንስት ፆታዎች ይገኛሉ። እነዚህ ፆታዎች በየራሳቸው ዘርን ማስተላልፍ የሚችሉብት ልዮ የማዳቀያ ህዋሳትን በአካላቸው ወስጥ ይሠራሉ ወይንም ያዘጋጃሉ።

የተባእት ተስለክላኪ ዘር ህዋስ፣ ከእንስቷ ፍሬ ዘር ህዋስ ጋር፣ በእንስቷ አካል ውስጥ ሲገናኙ:

እነዚህ ልዮ ህዋሳት 'ጋሜት' (gametes) በመባል ይታወቃሉ። እነዚህ ልዩ ህዋሳት በአካልቸው ተመሳሳይ (በተለይ isogametes በመባል የሚታወቁት) ሊሆኑ ቢችሉም፣ ነገር ግን በአብዛኛው ጊዜ ከተባእትና እንስት የሚገኙት የዘር ህዋሳት በቅርፃቸውም ሆነ በአኳኋናቸው ይለያያሉ። የወንዱ የዘር ህዋስ፣ ም'ጥን ያለና በትንሽ ይዘት ብዙ ዘራዊ ምልክቶችን ማጨቅ እንዲችል ሆኖ የተሠራ ሲሆን፣ ይህንንም ይዞ ረጅም ርቀት መጓዝ እንዲችል የፈሳሽ ውስጥ ተስለክላኪነት ባህርይ ወይንም ችሎታ አለው። የሴቷ ልዩ ህዋስ፣ ከወንዱ ህዋስ ጋር ሲስተያይ በአካሉ አንጋፋ ሲሆን፣ ይህ የሆነበትም ምክንያት ተንቀሳቃሽ ሳይሆን የረጋ ከመሆኑም ሌላ፣ ከተባእት ዘር ጋር ከተገናኘ በኋላ በውስጡ ለሚፈጠረው ሽል አስፈላጊውን የማፋፊያ ንጥረ ነገር መያዝ ስላለበት ነው።

የአንድ ፍጡር ፆታ የሚታወቀው በሚፈጥረው የዘር ህዋሥ አይነት ነው። ተባእት ፍጡራን የተባእትን የዘር ህዋሥ (spermatozoa, or sperm) ሲፈጥሩ፣ እንሥት ፍጡራን የእንሥትን የዘር ህዋሥ (ova, or egg cells) ይፈጥራሉ። የተወሰኑ ዝርያዎች፣ የተባእትንም የእንስትንም የዘር ህዋሥ ከአንድ ግላዊ አካል የሚያፈልቁ ሆነው ይገኛሉ። እነዚህ ፍናፍንት (hermaphroditic) በመባል ይታወቃሉ።

አብዛኛውን ጊዜ የአንድ ዝርያ ተቃራኒ ፆታዎች፣ የተለያየ የአካል ቅርፅና የባህርይ ገጽታ ይታይባቸዋል። ይህ ልዩነት ሁለቱ ፆታዎች ያለባቸውን የእርባታ ኃላፊነትና የሚያስከትለውን አካላዊ ተፅእኖ ያንፀባርቃል።

ወሲባዊ እርባታ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
በወሲባዊ ዘይቤ የሚራቡ ፍጡራን ህልውና፣ በህፕሎይድና በዳፕሎይድ ደረጃዎች ውስጥ ማለፍ አለበት

ይህ ተግባር፣ ከላይ እንደተጠቀሰው፣ የእንስትና የተባእትን ዘር በማዋኃድ ወይንም በማዳቀል፣ ፍጡራን ዝርያ (Species)፣በተዋልዶ ከአሮጌ ወደ አዲስ እየተታደስ፡ በቅጥልጣይ ረገድ ለረዥም ጊዜ እንዲቆይ የሚያስችል፣ ተፈጥሯዊ ተግባር ነው። በዘር ሀዋሣት ውህደት ወቅት ክሮሞሶም (Chromosomes) ከአንዱ ለጋሽ (ወላጅ) ወደሌላው ይተላለፋል። እያንዳንዱ ተሣታፊ ህዋሥ የለጋሾችን ግማሽ ክሮሞሶም ይይዛል። ግማሽ የአባት፣ ግማሽ የእናት ክሮሞሶሞች ተገናኛተው ይዋሃዳሉ ማለት ነው። ተወራሽ የዘር ምልክቶች፣ ዲ-አክሲ-ሪቦ-ኒውክሊክ አሲድ ወይንም ዲ-ኤን-ኤ (deoxyribonucleic acid (DNA)) በመባል በሚታወቀው፣ በክሮሞሶሞች ውስጥ የሚገኝ ንጥረ ነገር ውስጥ ሰፍረው ይገኛሉ። ይህ ውህደት ክግማሽ የአባት፣ ክግማሽ የእናት ክፍል የተስራ የክሮሞሶም ጥማድ ይፈጥራል። ክሮሞሶሞች በጥንድ ሆነው በሚገኙበት ጊዜ ዳይፕሎይድ (diploid) ይባላሉ። ክሮሞሶሞች በአሃዳዊ ህላዌ ጊዜ ሃፕሎይድ (haploid) ይባላሉ። ዳይፕሎይድ የሃፕሎይድ ህዋስን (ጋሜት (gametes)) መፍጠር ይችላሉ። ይህ የሃፕሎይድ ጥንሰሳ ሂደት ሚዮሲስ (meiosis) በመባል ይታወቃል። ሚዮሲስ የሚባለው ሂደት የክሮሞሶማዊ ቅልቅል (chromosomal crossover) ሁኔታን ሊፈጥርም ይችላል። ይህ ሁኔታ መሳ በሆኑ ክሮሞሶምች መካከል የሚፈፀም ሲሆን፣ የክሮሞሶሙ ዲ-ኤን-ኤ ከባቢ ተቆርሶ ከሁለተኛው ክሮሞሶም ዲ-ኤን-ኤ ከባቢ ጋር ይዋሃዳል። ተራፊዎቹ ዲ-ኤን-ኤ እርስ በርሳቸው ባኳያቸው ይዋሃዳሉ። ውጤቱም በባህርይ ከበኩር ዳይፕሎይድ የተለየ አዲስ ዳይፕሎይድ መፍጠር ነው። ይህ የክሮሞሶም ቅልቅል ሂደት ከለጋሽ ወላጆች በተፈጥሮ ባህሪው የተለየ አዲስ ዝርያ (Species) ይከስታል።

በብዙ ፍጡራን የርቢ ሂደት ውስጥ የሀፕሎይድ ክስተት፣ ጋሜት በመፍጠር ላይ ብቻ ያተኮረ ነው። በዚህ ሁኔታ የሚገኙት ጋሜት እርስ በርሳቸው በመቀላቀል ዳይፕሎይድ መከሰት እንደሚችሉ ሆነው የተዘጋጁ ናቸው። እንዲሁም በሌሎች ፍጡራን ርቢ ጊዜ ጋሜት ራሳቸውን በመክፈል አዲስና ልዩ ልዩ የአካል ህዋሣትን መፍጠር ይችላሉ። እነዚህ በዚህ ሁኔታ የሚፈጠሩ የአካል ህዋሣት ሃፕሎይድ ክሮሞሶም ይኖሯቸዋል። በሁለቱም በኩል የሚገኙት ጋሜት በውጭ አካላቸው ተመሣሣይነት ያሳያሉ። ሆኖም ግን በአካላቸው የማይመሳሰሉ ጋሜት ይገኛሉ። በተለምዶ ተለቅ ያሉት ጋሜት የእንስት ህዋስ (ovum, or egg cell) ሲሆኑ፣ አነስ ያሉት ደግሞ የተባእት ህዋስ (spermatozoon, or sperm cell) ናቸው። በአካል መጠን ተልቅ ያለ ጋሜት የሚያመነጭ ግለፍጡር የእንስትነትን ፆታ ይይዛል፣ እንዲሁም አነስ ያለ ጋሜት የሚያመንጭ ግለፍጡር የተባእትን ፆታ ይይዛል። ሁለቱንም አይነት ጋሜት በአካሉ ውስጥ የሚያመነጭ ግለፍጡር ፍናፍንት (hermaphrodite) ይባላል። በአንዳንድ ሁኔታ hermaphrodite ራሳቸውን በራሳቸው በማዳቀል፣ ያላንዳች ወሲባዊ ጓደኛ አዲስ አካል (ፅንሥ) መፍጠር ይቸላሉ ።

የዝንቦች የአየር ላይ ወሲባዊ ግንኙነት ትእይንት።

አብዛኞቹ የወሲባዊ ተራቢ እንስሳት እንድሜያቸውን የሚያሳልፉት በዳይፕሎይድነት ነው። በነዚህ እንሥሣት ውስጥ የሃፕሎይድ መኖር ጋሜትን ለመከሰት ብቻ የተዋሰነ ነው። የእንስሳት ጋሜት የእንስትና የተባእት ህላዌ አልቸው። እነዚሀም የተባእት ህዋስ እና የእንሥት ህዋስ (spermatozoa and egg cells) የሚባሉት ናቸው። ጋሜት በእንስቷ አካል ውስጥ በመዳቀል (በመዋኃድ) ከወላጅ ለጋሾች ዘር የተዋጣና፣ የታደስ አዲስ ፍጡር ወይንም ፅንስ (embryo) ይፈጥራሉ።

የወንዱ ጋሜት፣ የተባእት የዘር ህዋሥ (spermatozoan) በወንዱ ቆለጥ ወስጥ የሚጠነሰስ ሆኖ፣ በመጠኑ አነስተኛና በፈሳሽ ውስጥ ለመስለክለክ የሚያስችለው ጭራ አለው። ይህ የዘር ህዋስ ከሌሎች የአካል ህዋሳት ጋር ሲነፃፀር አብዝኛዎቹ መደበኛ ህዋሳዊ ክፍሎች የተሟጠጡበትና፣ ለፅንሥ ምስረታ ብቻ የሚያስፈልጉ ነግሮችን የያዘ ህዋስ ነው። የህዋሱ አካላዊ ቅርፅ፣ በፈሳሽ ውስጥ በፍጥነትና በቀላሉ እንዲጓዝ የተገነባ ነው።

የእንስት የዘር ህዋስ ፍሬያዊ ወይንም የእንቁላል ህዋስ ሲሆን በእንስቷ ማህፀን ውስጥ፣ እንቁላል እጢ ወይንም እንቁልጢ(ovaries) በሚባሉ ቦታዎች ውስጥ የሚጠነሰስ ነው። ይህ የዘር ህዋስ፣ ከተባእት የዘር ህዋስ ጋር ሲነጻጸር በአካሉ ትልቅ ሲሆን፣ የእንቁላል ወይንም የፍሬ ቅርፅ ይኖረዋል። በውስጡም ለመጸነሻ የሚያስፈልጉ የዘር ክሮሞሶሞችና፣ ጽንሱም ከተፈጠረ በኋላ አስፈልጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ከሚይዙ ክሌሎች ህዋሳት ጋር የተቆራኘ ሆኖ ይገኛል ። ሁሉም በአንድ እሽግ እንቁላል ውስጥ ይገኛሉ። የአጥቢ እንሥሣት ፅንስ በእንስቷ ውስጥ ለውልድ እስኪበቃ ድረስ ያድጋል። የሚያስፈልጉትን ንጥረ ነገሮችም ከእናቲቱ አካል በቀጥታ ይካፈላል።

እንሥሣት በአብዛኛው ተንቅሳቃሽ ሲሆኑ፣ የወሲባዊ ጓደኛ ወይንም አጣማጅ ይፈልጋሉ፣ ያስሳሉ። አንዳንድ በውሃ ውስጥ ይሚኖሩ እንሥሣት ውጫዊ ድቅለት (external fertilization) የሚባለውን ይጠቀማሉ። በዚህ ጊዜ የንእንስቷ እንቁላሎችና የተባእቱ የዘር ህዋስ ውኃው ውስጥ አንድ ላይ ተለቀው እንዲቀላቀሉ ይደረጋል። በመሬት ላይ የሚኖሩ እንሥሣት ግን የወንዱን የዘር ህዋሳት ወደሴቷ ሰውነት የማስተላልፍ ዘዴ ይጠቀማሉ። ይህ ውስጣዊ ድቅለት (internal fertilization) ይባላል።

አእዋፍ፣ አብዛኞቹ ለሠገራ፣ ለሽንት እንዲሁም ለመዳቀል የሚጠቀሙበት አንድ ብቸኛ ቀዳዳ አላችው። ይህ ሬብ (cloaca) ይባላል። ተባእትና እንስት አእዋፍ፣ ሬባቸውን በማገናኘት ወይንም በማጣበቅ የወንዱን ነባዘር (sperm) ያስተላልፋሉ። ይህ ሬባዊ ጥብቀት (cloacal kissing) በመባል ይታወቃል። አብዛኞቹ የመሬት ላይ እንሥሣት የወንዱን ነባዘር ለማስተላለፍ ይሚጠቅም ብልት ይኖራቸዋል። ይህ ብልት፣ ተስኪ ብልት (intromittent organ) በመባል ይታወቃል። በሰብአውያንና በአጥቢ እንሥሣት ውስጥ ይህ ብልት፣ ቁላ ተብሎ የሚታወቀው ነው። ይህ ብልት በእንስቷ የድቅያ ቀጣና (እምሥ) ውስጥ በመግባት የወንዱን ነባዘር ያፈሳል። ይህ ሂደት ወሲባዊ ግንኙነት (የግብረ ሥጋ ግንኙነት) ይባላል። የወንዱ ብልት፣ የወንዱ ነባ ዘር የሚያልፍበት የራሱ ቀጣና ይኖረዋል። የእንስት አጥቢ እንሥሣት ወሲባዊ ብልት (እምሥ) ከማህፀኗ ጋር የተገናኘ ነው። የሴቷ ማህፀን ፅንሱን በውስጡ በማቀፍ አስፈላጊ ንጥረ ነገሮችን ከሴቷ አካል እያንቆረቆረ፣ አቅፎ ጠብቆ ለውልድ እስኪበቃ ያሳድገዋል። ይህ ሂደት እርግዝና ይባላል።

በተንቀሳቃሽነታቸው ምክንያት፣ የአንዳንድ እንሥሣት ድቅለት የግዳጅ ወሲብን ይከስታል። አንዳንድ ነፍሳት ለምሳሌ፣ የእንስቷን ሆድ በመቅደድ ወሲብ ያካሂዳሉ። ይህ እንስቷን የሚያቆስል ብቻ ሳይሆን፣ የሚያሰቃይ ነው።

አበቦች የአባቢ እፅዋት የወሲብ ብልት ሊባሉ ይችላሉ። አብዛኛውን ጊዜ አበቦች ሁለቱንም ፆታዊ ክፍሎች በውስጣቸው ይይዛሉ።

እንደ እንሥሣት፣ ዕፅዋትም የእንስትና የተባእት የዘር ህዋስ (gamete) ያመነጫሉ። ብዙ ታዋቂ የሆኑ ዕፅዋት የሚያመነጩት ተባእታይ የዘር ህዋስ በቅርፊት የታቀፈ ሆኖ በናኒ ወንዴዘር(pollen)ይባላል።

የእፅዋት እንሥት የዘር ህዋስ በኦቭዩል ውስጥ የሚገኝ ነው። ይህ እንስታይ ህዋስ፣ በወንዱ ወንዴዘር ከተደቀለ በኋላ የእፁን ዘር (seed) ያመነጫል። ይህ ዘር እንደ እንቁላል በውስጡ ለሚፈጠረው ፅንሥ አስፈላጊ ንጥረ ነገር ይይዛል።

እንስት (በግራ) እና ተባእት (በቀኝ) ሆነው የሚታዩት ፍሬ መሰሎች፣ የዝግባና የመሳሰሉት ስርክ-አበብ ትልልቅ ዛፎች የሴትና የወንድና ወሲባዊ ብልቶች ናቸው

ብዙ ዕፅዋት አ'ባቢዎች ናቸው፣ ማለትም አበቦችን ያወጣሉ። አበቦች የዕፅዋቱ ወሲባዊ ብልቶች ናቸው። አበቦች አብዛኛውን ጊዜ ፍናፍንት (hermaphroditic) በመሆናቸው፣ የሁለቱንም ፆታዎች (የወንድና የሴት) የዘር ህዋሳት ይይዛሉ። በአበባው መሃል ካርፔል (carpel) ይገኛሉ። ከነዚህ አንዱ ወይንም በዛ ያሉት ተጣምረው ፒስቲል (pistil) ይሰራሉ። በፒስቲል ውስጥ የእንስት ፍሬ ወይንም ዘር ማመንጫ ኦቭዩል (ovule) ይገኛሉ። ኦቭዩል ከተባእት የዘር ሀዋስ ጋር ሲዳቀሉ ዘር (seed) ያመነጫሉ። የአባባው ተባእት ክፍሎች ስቴምን (stamen) ይባላሉ። እነዚህ ጭራ መሰል ተርገብጋቢዎች በአባባው ዛላና (petal) በፒስቲል ውጫዊ ዙሪያ የሚገኙ ሲሆኑ፣ ጫፋቸው ላይ በውስጣቸው የተባእትን የዘር ህዋስ የሚይዙ የንፋስ በናኒዎች "ወንዴዘር"(pollen) ማመንጫ ክፍሎች አሏቸው። አንድ የወንዴዘር ረቂቅ በካርፔል ላይ ሲያርፍ፣ የእፁ ውስጣዊ ክፍል እንቅስቃሴ በማድረግ ረቂቁን በካርፔል ቀጣና ውስጥ በማሳለፍ ከኦቭዩል ውስጥ እንዲገባና እንዲዋሃድ ይደረጋል። ይህ ውህደት ዘር (seed) ይፈጥራል።

ዝግባና መስል ሰርክ አበብ ዛፎች አና ዕፅዋት፣ የተባእትና የእንስትነት ህላዌ የሚይዙ ፍሬ መሰል (cone) አካሎች አሏቸው። በብዛት ሰው የሚያቃችው ፍሬ-መሰል (cone) አብዝኛውን ጊዜ ጠንካራ ሲሆኑ በውስጣቸው ኦቭዩል አሏቸው። የተባእት ፍሬ-መሰል አነስ ያሉ ሲሆኑ በናኒ ወንዴዘር (pollen) አመንጪዎች ናቸው። እነዚህ በናኒዎች በንፋስ በንነው ከእንስቱ ፍሬ-መሰል ላይ ያርፋሉ። አበቦች ላይ እንደሚታየው ሁኔታ፣ እንስታዊ ፍሬ-መሰል ከተባእት ወንዴዘር ጋር ከተዳቀሉ ዘር ያመነጫሉ።

እፅዋት በአንድ ቦታ የረጉ በመሆናቸው፣ ደቂቅና በናኒ ወንዴ የዘር ህዋሳትን ወደ እንስታን ክፍል ለማስተላለፍ የተለያዩ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ። ከነዚህ ውስጥ ለመጥቀስ ያክል፣ ሰርክ አበብ ዛፎችና የሳር አይነቶች፣ ደቂቅና ብናኝ የሆኑ የወንዴዘሮችን በማዘጋጀት በንፋስ ተሽካሚነት ወደ እንስት ክፍሎች እንዲደርሱ ያደርጋሉ። በዚህ ጊዜ የአንድ ሳር ወይንም ዛፍ ወንዴዘር ወደጎረቤት ሳር ወይንም ዛፍ የእንስት ክፍሎች በመድረስ ሊዳቀል ይችላል። ሌሎች እፅዋት ደግሞ ከበድ ያሉ ተጣባቂ ወንዴዘሮችን ያዘጋጃሉ። እነዝህ እፅዋት በነፍሳት ላይ የሚመካ አቅርቦትን ይጠቀማሉ። እነዚህ እፅዋት በአበቦቻችው ውስጥ የሚያመነጩት ጣፋጭ ፍሳሽ ብዙ ነፍሳትን የሚስብ ወይንም የሚማርክ ነው። ነፍሳቱ፣ ለምሳሌ ቢራቢሮዎችና ንቦች ይህንን ጣፋጭ ለመቅሰም ከአበባው ላይ ያርፋሉ። በዚህ ጊዜ ተጣባቂ ወንዴዘር ከነፍሳቱ እግሮች ላይ ይጣበቃሉ። ነፋሳቱም ብናኞቹን በእግሮቻቸው በመሸከም ወደ ሌላ ተክል በመውሰድ ከእፁ እንስታዊ ክፍሎች ላይ ያደርሷቸዋል።

በተጨማሪ፣ ብዙ የአትክልት አይነቶች ወሲባዊ በማይሆን ዘዴ መስፋፋትና መባዛት ይችላሉ። ይህ እፃዊ ተዋልዶ ይባላል። ለምሳሌ ከአንድንድ የፍራፍሬ ዛፍ (እንደ በለስ) አንድ ቅርንጫፍ ተወስዶ ከአዲስ መሬት ቢተከል፣ ይህ ቅርንጫፍ ያለ ወሲብ አዲስ 'ሕጻን' ዛፍ ሊሆን ይችላል።

ፈንጋይ (fungii)

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
የጅብ ጥላ የሚራባው በፈንጋይ ወሲባዊ ርባታ ዘዴ ነው

አብዛኞቹ በወሲባዊ ዘዴ የሚራቡት ፈንጋይ፣ የህልውና ሂደታቸው በሃፕሎይድና ዳይፕሎይድ ደረጃ ውስጥ ያልፋል። ፈንጋይ በአብዛኛው ፍናፍንትነትን (isogamous) የሚያሳዩና፣ ለእንስትነትና ለተባእትነት የተወሰኑ ፆታዎች የሏቸውም። የፈንጋይ ሃፕሎይድ አንዱ ከሌላው የሚያቀራርብ አካላዊ እድገት ያሳዩና፣ በመጨረሻው ሙሉ በሙሉ በመገናኘት የዘር ህዋሶቻቸውን ያዋህዳሉ። አንድአንድ ጊዜ ይህ ውህደት ሙሉ በሙሉ በአካል የተስተካከለ ሳይሆን የተዛባ (asymmetric) ነው። በዚህ ወቅት፣ ህዋሳዊ ክሮሞሶም ብቻ የሚያቀርበውና አስፈላጊ ንጥረነገሮችን የማያዋጣው ሃፕሎይድ ተባእት ሊባል ይችላል የሚል የሚመጥን ሃሳብ ማቅረብ ይቻላል።

የአንድአንድ ፈንጋይ ወሲባዊ ሂደት፣ (ለምሳሌ እርሾ ውስጥ የሚገኙት) የወንድና የሴትነት ተዋናይነትን የሚይዙ ጥንዶችን ይፈጥራል። የእርሾ ፈንጋይ አንዱ ሃፕሎይድ ከተመሳሳይ ሃፕሎይድ ጋር አይዋሃድም። ይህም ማለት የመምረጥ ዝንባሌ እያሳየ ከራሱ ተቃራኒ የሆነ ሃፕሎይድ ጋር ብቻ ይዋሃዳል። የዚህ ጥምረት ተዋንያን የወንድነትና የሴትነት ህላዊ አላቸው ለማለት ይቻላል።

የአንዳንድ ፈንጋይ ወሲባዊ ሂደት ዕፅ መስል አካላዊ ደረጃዎችን ይፈጥራል። ላምሳሌ የጅብ ጥላ (mushroom) በመባል የሚታወቀው፣ የፈንጋይ ወሲባዊ ሂደት ክፍል ነው። የጅብ ጥላ የሚፈጠረው፣ የዳይፕሎይድ ክስተት በፍጥነት የመከፋፈል ሂደት ውስጥ ሲያልፍ ነው። ይህ ክፍፍል ወይንም ሚዮሲስ የሃፕሎይድ ስፖር (spores) ይፈጥራል። እነዚህ የመብነን እድላቸውን ለማብዛት ከመሬት ወጥተው ያድጋሉ ወይንም ይረዝማሉ። ይህ ሂደት ጥላ መስል ቅርፅ ይይዛል።

ዝግመተ ለውጥ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ወሲብ የፍጡራን ተመራጭ ገፅታ በድቅለት እንዲሰራጭ ይረዳል። የሚታየው ምስል በወሲባዊ ፍጡር ውስጥ የሚገኙ የዘር ምዝግቦችን (allele) የተደጋጋሚነት ዝግምተ ለውጥ የሚያመዛዝን ነው። (a) እና ኢወሲባዊ መንጋ (b). ቋሚው አምድ ድግምጋሚን ሲያሳይ አግዳሚው አምድ የጊዜ ሂደትን ያሳያል። a/A እና b/B የሚባሉት የዘር ምዝግቦች ህላዊነታቸው አቦሰጥ ነው። ተፈላጊው ዘራዊ ገፅታ AB ከ (a) ዳግም ውህደት በኋላ ብፍጥነት ይሰራጫል, ሆኖም ግን ከ(b) ውስጥ ራሱን ችሎ መከስተ አለበት.

ወሲባዊ እርባታ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተው ከአንድ ቢሊዮን አመታት በፊት እንደሆነ ይገመታል። የወሲብ ክስተት አሃዳዊ ህዋስነት ካላቸው ዩክሮይት(eukaryotes)ከሚባሉ ደቂቅ ህላውያን የመነጨ ነው። የወሲባዊ እርባታ ክስተት እንዲሁም እስክጊዜያችን የመዝለቁ ጉዳይ አከራካሪና እልባት ያልተገኘለት ጉዳይ ነው። አንዳንድ መጣኝ መላምቶች የሚከተሉትን ይመስላሉ፤ ወሲብ ፅንሶቹ የተለያየ ዘራዊ ባህርይ እንዲኖራቸው ያግዛል፣ ወሲብ ጠቃሚ የዘር ገፅታዎች እንዲሰራጩ ይረዳል፣ ወሲብ የማይጠቅሙ ገፅታዎች እንዳይሰራጩ ይረዳል፣ የሚሉት ይገኙበታል።

ወሲባዊ እርባታ ዩክሮይት ብቻ የሚጠቀሙበት ዘዴ ነው። ዩክሮይት፣ በውስጣቸው ማዕከላዊ (nucleus)እና ከባቢ (mitochondria)ያሏቸው ህዋሳት ናቸው። ከእንሰሳት በተጨማሪ፣ ዕፅዋት እና ፈንጋይ እንዲሁም ሌሎች ዩክሮይት (ምሣሌ፣ የወባ ነቀዝ) ወሲባዊ እርባታን ይጠቀማሉ። አንዳንድ ደቂቅ ህላውያን ለምሳሌ ባክቴርያ አካላዊ ውህደት (conjugation)የሚባለውን ድቀላ ይጠቀማሉ። ይህ ድቀላ ወሲባዊ ባይሆንም የዘር ምልክቶች እንዲዳቀሉና አዲስ ፅንስ እንዲፈጠር ይረዳል።

ወሲባዊ እርባታን ወይንም ወሲባዊ ድቅለትን ያረጋግጣል ተብሎ የሚታመነው ክስተት የጋሜት ልዩነትና የድቀላው አሃዳዊነት ናቸው። በአንድ ዝርያ የተለያዩ ጋሜት መኖራቸው እንደ ወሲባዊ ድቅለት ቢቆጠርም፣ በህብረ ህዋስ እንሥሣት ውስጥ ሳልሳዊ ጋሜት ስለመኖሩ የሚታወቅ ነገር የለም።

የስብአዊ ፍጡር ርባታ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የሰብእን ሥነ ፍጥረታዊ እርባታ በተመረኮዘ ወደፊት ራሱን የቻለ አምድ ይዘጋጃል። ለጊዜው ይህ ርዕስ ተንገዋሏል።

በፍጡራን ውስጥ መደበኛው የፆታ አይነት ፍናፍንት (hermaphrodites) የሚባለው ለምሳሌ የቅንቡርስና የአብዛኞቹ እፅዋት ይዘት ነው። በዚህ የፆታ አይነት አንድ ግላዊ ፍጡር ሁለቱንም ተቃራኒ የፆታ አይነቶች ማለትም የተባእትና የእንስትን የዘር ህዋሳት ያመንጫል። ሆኖም ግን ብዙ ዝርያዎች በፆታችው አኃዳዊ የሆኑ ግላውያንን ያዘጋጃሉ። ማለትም እነዚህ ግላውያን የዝርያውን እንስታዊ ብቻ ወይንም ተባእታዊ ብቻ ፆታ ይይዛሉ። የአንድን ግላዊ ፍጡር ፆታ የሚወስነው ሥነፍጥረታዊ ሂደት፣ ፆታ መወሰኛ (sex determination)በመባል ይታወቃል።

የተወሰኑ ፍጡራን ለምሳሌ እንደቀይ ትል ያሉት ፆታዎቻቸው የፍናፍንትነትና የተባእት ይዘት አላቸው። ይህ ዘዴ አንድሮዳዮሲ (androdioecy)ይባላል።

አንዳንድ ጊዜ በአንድ ፅንስ እድገት ሂደት ጊዜ ሽሉ በሴትነትና በወንድንት ማእከል ውስጥ ያለ ይሆናል። ይህ ሁኔታ ድብልቅ ፆታ (intersex) ሲባል፣ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ግላዊ ፍጡራን ፍናፍንት ሊባሉ ይችላሉ። ሆኖም ግን እንዚህ ፍጡራን ያልተለመዱ ናቸው ምክንያቱም በሴትነትም ሆነ በወንድንት ሙሉ በሙሉ ያልዳበሩ በመሆናቸው ነው።

ዘረ መልአዊ (Genetic)

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
እንደ ስብኣውዊ ፍጡር እና ሌሎች ኣጥቢ እንስሳት፣ ዝንቦች የ 'XY' ዖታ መወሰኛን ዘይቤ ይጠቀማሉ።

በዘረ መልአዊ መወሰኛ ዘይቤ፣ የአንድ ግላዊ ፆታ የሚወሰነው በሚወርሰው የዘርምል (genome)ነው። የዘረ መልአዊ ፆታ መወሰኛ ዘይቤ በተዛባ ሁኔታ የሚወረስ፣ የክሮሞሶማዊ ውህደት ላይ የተመረኮዘ ነው። እነዚህ ክሮሞሶሞች በውስጣቸው የፆታን ክስተት የሚወስኑ የዘር ምልክቶች ይይዛሉ። የፅንሱ ፆታ የሚወሰነው ባሉት የፆታ ክሮሞሶም አይነቶች ወይንም በሚገኙት ክሮሞሶሞች ብዛት ነው። የዘረ መልአዊ ፆታ ውሳኔ በክሮሞሶማዊ ውቅረት ላይ የተመረኮዘ ስለሆነ፣ አብዛኛውን ጊዜ የሚፀነሱት የተባእትና የእንስት ፅንሶች ቁጥር በብዛት አኳያ ሲታይ ተመጣጣኝ ነው።

ሰብዓውያንና ሌሎች አጥቢ እንስሳት የ 'XY' የፆታ መወሰኛ ዘዴን ይጠቀማሉ። 'Y' ክሮሞሶም የወንድ ፅንስ እንዲፈጠር የሚያግዙ ማነሳሻ ነገሮችን ይይዛል። የ 'Y' ክሮሞሶም በሌለ ጊዜ በመደበኝነት የሚከሰተው ፅንስ እንስት ይሆናል። ስለዚህ 'XX' ኣጥቢ እንሥሣት እንስት ሲሆኑ 'XY' የሆኑት ደግሞ ተባዕት ናቸው። የ 'XY' ፆታ መወሰኛ ዘይቤ በሌሎች ፍጡራን ለምሣሌ በዝንቦችና በእፅዋት ውስጥ ይገኛል። አንዳንድ ጊዜ፣ ለምሳሌ በዝንቦች ውስጥ የፆታ ወሳኝ የሚሆነው የ 'Y' ሳይሆን የ'X' ክሮሞሶም ነው።

አእዋፍ የ'ZW' ፆታ መወሰኛ ዘይቤ ሲኖራቸው ከላይ ከተጠቀሰው የተገላቢጦሽ ሁኔታ ይታይባቸዋል። የ'W' ክሮሞሶም የእንስትን ፅንስ መ'ከሰት የሚያነሳሱ ነገሮችን ሲይዝ መደበኛው ፆታ ግን ወንድ ነው። በዚህ ሁኔታ ZZ ግላውያን ተባእታን ሲሆኑ፣ 'ZW' ደግሞ እንስታን ናቸው። ብዙ በራሪዎች፣ ቢራቢሮዎችን ጨምሮ የ'ZW' የፆታ መወሰኛ ዘዴን ይከተላሉ። ባየናቸው የ 'XY' እና 'ZW' ፆታ መወሰኛ ዘይቤዎች ውስጥ የፆታ መወሰኛው ክሮሞሶም በአካሉ በአብዛኛው አናሳ ሲሆን የፆታ መወስኛና ማነሳሻ ምልክቶችን ከመያዙ በስተቀር ሌሎች ነገሮች በውስጡ በብዛት አይኖሩም።

ሌሎች ነፍሳት ደግሞ የሚከተሉት የፆታ መወሰኛ ዘይቤ ባላቸው የክሮሞሶም ብዛት ላይ የተመረኮዘ ነው። ይህ XX/XO ፆታ መወሰኛ ዘይቤ ይባላል። 'O' የፆታ መወሰኛ ክሮሞሶም አለመኖርን ያመላክታል። በነኝህ ፍጡራን ውስጥ ያሉት ክሮሞሶም ዳይፕሎይድ ሲሆኑ፣ ሆኖም ግን አንዳንዶቹ አንድ ወይንም ሁለት 'X' ክሮሞሶም ሊወርሱ ይችላሉ። በፌንጣዎች ለምሳሌ አንድ 'X' ክሮሞሶም የሚወርሰው ፅንስ ወንድ ሲሆን፣ ሁለቱን የሚወርሰው ደግሞ ሴት ይሆናል። nematode C. elegans በሚባሉት ትሎች ውስጥ አብዛኞቹ ራስ በራስ ተዳቃዮች 'XX' ፍናፍንቶች ሲሆኑ አልፎ ደግሞ በክሮሞሶም ውርሰት ውዝግብ ምክንያት 'X' ክሮሞሶም ብቻ ያላቸው ግላውያን ሊፈጠሩ ይችላሉ። እነኝህ 'XO' ግላውያን ተራቢ ተባእት ይሆናሉ። (ከሚፀንሷቸው ፅንስ ግማሾቹ ተባእት ይሆናሉ።)

ሌሎች ነፍሳት፣ ለምሳሌ ንቦችና ጉንዳኖች haplodiploid የሚባለውን የፆታ መወሰኛ ዘይቤ ይጠቀማሉ። በዚህ ጊዜ ዳይፕሎይድ የሆኑት ግላውያን በአብዛኛው እንስት ሲሆኑ፣ ሃፕሎይድ ይሆኑት (ከተደቀለ እንቁላል የሚያድጉት) ደግሞ ተባእት ናቸው። ይህ የፆታ መወሰኛ ዘይቤ፣ በቁጥር ረገድ ወዳንዱ ፆታ ዝንባሌ ላለው የፆታ ስርጭት ይዳ'ርጋል። የህ የሚሆንበት ምክንያት የፅንሱ ፆታ የሚወሰነው በድቅለት ጊዜ እንጂ በሚዮሲስ ጊዜ በሚከሰተው ክሮሞሶማዊ ይዘት አለመሆኑ ነው።

ኢ-ዘረመልአዊ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ክላውን አሶችClownfish ከጅምሩ ተባእት ሲሆኑ ከከባቢ ካሉት ሁሉ በአካሉ አንጋፋ የሆነው ግላዊ የእንስትነትን ፆታ ይይዛል።

በዘረ መልአዊ የፆታ ውሳኔ የማይጠቀሙ፣ ነገር ግን የከባቢ ተፈጥሮን ፀባዮች የሚመረኮዝ ፆታዊ ውሳኔ ያላቸው ብዙ ፍጡራን አሉ። ብዙ ደመ ቀዝቃዛ፣ ገበሎ-አስተኔ (reptile)ፍጡራን የከባቢ ሙቀት ላይ የተመረኮዘ የፆታ መወሰኛ ዘዴ ይጠቀማሉ። ፅንሱ በእድገቱ ጊዜ የሚሰማው ከባቢ ሙቀት የሽሉን ፆታ ይወስናል። ለምሳሌ በአንዳንድ የኤሊ አይነቶች ውስጥ ፅንሱ በእርግዝና ጊዜ ከባቢው ቀዝቀዝ ያለ ከሆነ ሽሉ ተባእት ይሆናል። ይህ የፆታ መወሰኛ ሙቀት መጠን ወሰናዊ ዝልቀቱ ከ1-2°C አያልፍም።

ብዙ የአሳ ዘሮች በህልውናቸው ዘመን ፆታ የመለወጥ ፀባይ ይታይባቸዋል። ይህ ክስተት የቅደም ተከተል ፍናፍንትነት (sequential hermaphroditism) ይባላል። በአንዳንድ የአሳ አይነቶች በአካሉ አንጋፋ የሆነው ግለፍጡር እንስት ሲሆን፣ አናሳ የሆነው ደግሞ ተባእት ይሆናል። በሌሎች የአሳ አይነቶች ለምሳሌ 'wrasses' የዚህ የተገላቢጦሽ ሁኔታ ይታያል፣ ማለትም ግላውያኑ በወጣትነታቸው እንስት ሆነው ያድጉና ሲተልቁ የተባእትነትን ፆታ ይይዛሉ። እነዚህ ቅደም-ተከተላዊ ፍናፍንትነትን የሚከተሉት ፍጡራን የሁለቱንም ፆታዎች የዘር ህዋስ ወይንም ጋሜት በህይወት ዘመናቸው ጊዜ ማመንጨት ቢችሉም፣ በአንድ በተወሰነ ጊዜ ግን ወይ ሴቶች ናቸው ወይ ወንዶች ናቸው።

በአንዳንድ ትላልቅ ዛፎች በተለይ ፈርን (ferns)ተብለው በሚታወቁት ውስጥ መደበኛው ፆታ ፍናፍንትነት ነው፣ ሆኖም በቅድሚያ የፍናፍንትን ተክል ያበቀለ አፈር ላይ የሚያድጉት ግላውያን በሚያገኙዋቸው ትርፍራፊ ንጥረነገሮች ተፅዕኖ ምክንያት የተባእትነትን ፆታ ይዘው ያድጋሉ።

ፆታዊ የአካል ልዩነት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
የአንዳንድ አእዋፍ ዝርያዎች የፆታዊ አካል ልዩነት በመልክም በመጠንም አኳያ ይንፀባረቃል

ብዙ እንሥሣት በመልክም ሆነ በመጠን ልዩነት ያሳያሉ። ይህ ክስተት ፆታዊ የአካል ልዩነት (sexual dimorphism)በመባል ይታወቃል። ፆታዊ የአካል ልዩነት ከወሲባዊ ምርጫ (sexual selection)- ተመሣሣይ ፆታ ያላቸው ግላውያን ከተቃራኒ ፆታ ጋር ለመዳራት የሚያደርጉት ፉክክር- ጋር የተቆራኘ ነው። የአጋዘን ቀንድ ላምሣሌ፣ ወንዶቹ ከሴቶቹ ጋር የመዳራት እድል ለማግኘት ለሚያደርጉት ፍልሚያ ያሚያገለግል ነው። በአብዛኛው ዝርያ፣ የወንድ ፆታ አባሎች ከሴቶቹ በአካል ይገዝፋሉ። በአጥቢ እንሥሣት ውስጥ ክፍተኛ ፆታዊ የአካል ልዩነት ከአለ ከዚሁ ጋር ተያይዞ አንድ ወንድ ብቻውን ከብዙ ሴቶች ጋር የመዳራት ሁኔታ ይታያል። ይህም የሚሆነው በአካባቢው በሚገኙት ግላውያን ወንዶች መካከል በሚከስተው የጋለ የድሪያ መብት ማረጋገጫ ፍልሚያ ምክንያት ነው።

በሌሎች እንሥሣት፣ ነፍሳትንና አሦችን ጨምሮ፣ ሴቶቹ በአካል ከወዶቹ የሚገዝፉበትም ክስተት አለ። ይህ ሁኔታ የድቀላ እንቁላልን ከማዘጋጀት ጋር የተያያዘ ነው ለማለት ይቻላል። ቀድም ሲል እንደተወሳው የእንስትን የዘር ቅንቁላል ወይንም ፍሬ ማዘጋጀት፣የተባእትን የዘር ህዋስ ከማዘጋጅት ይልቅ ብዙ የንጥረነገር ቅምር ይጠይቃል። በአካል የገዘፉ እንስታን ብዙ የዘር እንቁላል መሥራት ይችላሉ። አንዳንድ ጊዜ ይህ ፆታዊ የአካል ልዩነት እጅግ የበዛ ከመሆኑ የተነሳ ወንዶቹ የሴቶቹ ጥገኛ በመሆን ብቻ ተወስነው እንዲቀሩ ያደርጋል።

በአእዋፍ ውስጥ ወንዶቹ በአብዛኛው በህብረቀለም የተዋቡ (ለምሣሌ እንደ ተባእት የገነት ወፍ) ሆነው ይታያሉ። ይህ ሁኔታ አንዳንድ ፍጡራንን ለኑሮ በጂ ያልሁነ ሁኔታ ላይ ይጥላቸዋል የሚል አመለካከት አለ። (ለምሣሌ ህብራዊ ቀለም አንድን ወፍ ለአጥቂዎች በግልፅ እንዲታይ ያደርገዋል) ከዚህ በተፃፃሪነት ደግሞ "የስንኩልነት ዘይቤ" (handicap principle)የሚባል አመለካከት አለ። ይህ አመለካከት ወንዱ ወፍ ራሱን ለአጥቂዎች አጋልጦ በማሳየቱ፣ ነገዳዊ ጥንካሬውንና ድፍረቱን ለሴቶቹ ይገልፃል ይላል።

ሰብአዊ ፍጡራን፣ ወንዶቹ አጠቃላይ የሰውነት ግዝፈትና የሰውነት ፀጉር በመያዝ እንዲሁም ሴቶቹ ተለቅ ያሉ ጡቶችን በማውጣት፣ ሰፋ ያሉ ዳሌዎችን በመያዝና ከፍ ያለ የውስጥ ሰውነት ቅባታዊ ይዘት በማፍለቅ የፆታ አካልዊ ልዩነትን ያሳያሉ።