ድቡልቡል ትል

ከውክፔዲያ
«ባለጸጋ አዲስ ዘንጌ ትል» ብዙ የተመራመረ የድቡልቡል ትል ዝርያ

ድቡልቡል ትል Nematoda የትም ቦታ የሚገኝ ጥቃቅን ትል ወይም ወስፋት ያሉበት የእንስሳት ክፍለስፍን ነው።

ድቡልቡል ትል በግለሰብ ቁጥርም ሆነ በዝርዮች ቁጥር (ምናልባት ፩ ሚሊዮን ዝርዮች) በፍጹም የሚበዛው ክፍለስፍን ነው። ከምድር ሕያዋን ሁሉ አብዛኞቹ ድቡልቡል ትል ናቸው። አብዛኞቹ ድቡልቡል ትል ደቂቅ ዘአካል ነው፤ አንዳንድ ዝርያ ግን በሰዎች እስከሚታይ ድረስ ትልቅ ይሆናል። አንዳንድም ዝርያ ችግር ሊፈጠር ሲችል «ወስፋት» ይባላል።

እጅግ ደቂቅ ዘአካል የሆኑት አይነቶች የትም ቦታ ይገኛሉ ሲባል ይህም በላይኛ አፈር፣ በውቅያኖስ፣ ወይም በሌላ ሕይወት ውስጥ አሉ ማለት ነው። በ1906 ዓም ሳይንቲስቱ ኔሰን ካብ እንዳለ፣

«ባጭሩ፣ በአለም ውስጥ ያለው ቁስ ሁሉ፣ ከድቡልቡል ትል በቀር፣ ወደ ሌላ አለም ቢጠረግ ኖሮ፣ አለማችን ደብዛዛ ሆኖ ሊታወቅ የሚችል ገና ቀርቶ ይሆን ነበር። እኛም፣ ሥጋ የሌለን መናፍስት ሁነን፣ ከዚያ ልንመርምረው ብንችል ኖሮ፣ ተራሮቹ፣ ኮረብቶቹ፣ ሸለቆቹ፣ ወንዞቹ፣ ሐይቆቹና ባሕሮቹ በድቡልቡል ትል ሰፈፍ ተወክለው እናገኛቸው ነበር። የመንደሮች ሥፍራ ሊፈታ ይችል ነበር፣ ለያንዳንዱ ሰዎች ስብስብ፣ በተመሳሳይ መጠን የድቡልቡል ትል ስብስብ ይኖር ነበርና። ዛፎች፣ መንገዳችንንና ጎዳናችንን ወክለው፣ በቅርጽ ተርታዎች ገና ይቆሙ ነበር። የተለያዩት አትክልትና እንስሶች ሥፍራ ገና ሊፈታ ይችል ነበር። በቂ ዕውቀትም ለኛ ቢኖረን ኖሮ፣ የቀድሞ ድቡልቡል ትል ተውሳኮቻቸውን በመመርመር ዝርዮቹም ስንኳ ብዙ ጊዜ ሊታወቁ ይቻል ነበር።»
ክሪኮኔማቲዴ የመሬት ትል ዝርያ ነው።