የውሃ ድብ

ከውክፔዲያ
የውሃ ድብ

የውሃ ድብውሃ ውስጥ የሚኖር የደቂቅ ዘአካል ክፍለስፍን (Tardigrada) ነው።

የውሃ ድብ መጀመርያ በማይክሮስኮፕ አማካኝነት በ1765 ዓም ተገኘ። አሁን ከአንድ ሺህ በላይ ዝርያዎች ታውቀዋል።

ቅርጹ እና አካሄዱ በተለይ እንደ ድብ ስለመሰለ ስለዚህ ስሙ «የውሃ ድብ» ተብሏል። የውሃ ድብ ስምንት ትንንሽ እጆች አሉት። እንስሳው ከአንድ ሚሊሜትር በላይ አይረዝሙም። የአትክልት ህዋስ ይበላል፤ አንዳንድም ዝርያ የእንስሳ ህዋስ (የሌላ ደቂቅ ዘአካል) ይበላል።

የውሃ ድብ በብዙ ቦታ በሳርንስት፣ በጨው አልባ ውሃ፣ በውቅያኖስም፣ ወይም በሂማላያ ተራሮች ጫፍ ቢሆንም ተገኝተዋል። ውሃ በያለበት ሁሉ ይኖራሉ።

የውሃ ድብ በማናቸውም ሁኔታ ያህል ሊኖር ይችላል። ያለ ውሃ፣ የውሃ ድብ ሰውነት ይደርቃል እንጂ ለብዙ አመት አይሞትም፣ በውሃ እንደ ተመለሠ እንደገና ሕያው ይሆናል። እጅግ ከፍተኛ ሙቀት ወይም ብርድ ውስጥ ሊኖር ይችላል። እንኳን በጠፈር ጉዞ ተልኮ በጠፈር ሊኖር ይችላል።

ውሃ ድብ