ቴምፕላርስ

ከውክፔዲያ
ቴምፕላሮች ማህተም — ሁለቱ ፈረሰኛች የክህነትንና የውትድርናን ሁለትዮ (duality) አመልካች እንደሆኑ ተደርጎ ይታመናል።

ቴምፕላር ወይም በሙሉ ስማቸው የክርሰቶስ እና የሰለሞን መቅደስ ምስኪን ወታደሮች የሚባሉት በጣም ታላቅ እና ሃይለኛ ከነበሩት ክርስቲያናዊ ወታደራዊ ስርአቶች ውስጥ ዋነኞቹ ናቸው። ይህ ስርዓት በ1088 ዓ.ም. ከተካሄደው አንደኛው የመስቀል ጦርነት በኋላ ማለትም በ1110 ዓ.ም. አዲስ የተቋቋመውን የእየሩሳሌም መንግስት ከእስላሞች ለመከላከልና ወደ ከአውሮፓ ወደ እየሩሳሌም የሚጎርፉትን ተሳላሚዎች ደህንነት ለመጠበቅ የተመሰረተ ነው።


አደረጃጀት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ቴምፕላሮች የተዋቀሩት በገዳማዊ ስርዓት ሲሆን ይኸውም የሲሰተርሲያን ስርዓት መስራች የነበረው የክላርቮው በርናርድ በዘረጋላቸው ህግጋት መሰረት ነው። ቴምፕላሮች ከብዙ መሳፍንት ጋር ግንኙነት ስለነበራቸው እና ጳጳሱም እነሱ ከሚቆጣጠሩዓቸው ቦታዎች ሁሉ ግብርና አስራት እንዲሰበስቡ ስለፈቀደላቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝነኛና ሃይለኛ ለመሆን ችለዋል።

ቴምፕላሮቹ አራት ዋና ክፍሎች የነበሩአቸው ሲሆን እነዚሁም፤

  • ዋነኞቹ ወታደሮች ወይም ናይትስ የሚባሉት፤ ሙሉ የፈረሰኛ ትጥቅ የታጠቁ
  • ከዝቅተኛ የህብረተሰቡ ክፍል የተውጣጡት ወይም ሰርጀንትስ በመባል የሚታወቁት፤ መለስተኛ የፈረሰኛ ትጥቅ የታጠቁ
  • ገበሬዎች፤ ዋነኛው ስራቸው የስርዓቱን ንብረት ማስተዳደር የነበረ እንዲሁም
  • ካህናት፤ ስራቸው የስርዓቱን መንፈሳዊ ህይወት መከታተል የነበረ ናቸው።


ታሪክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]