ቶኒ ኦርላንዶ ኤንድ ዳውን

ከውክፔዲያ
ቶኒ ኦርላንዶ እና ዳውን በ1974 እ.ኤ.አ.

ቶኒ ኦርላንዶ ኤንድ ዳውን (Tony Orlando and Dawn) በተለይ በአሜሪካ አገር በ1970ዎቹ እ.ኤ.አ. (1970-1977 እ.ኤ.አ. ወይም 1962-1970 ዓ.ም.) ዘመናዊ የሆነ ዘፋኝ ሙዚቃ ቡድን ነበሩ።

መሪው ዘፋኝ ቶኒ ኦርላንዶ ቡድኑን ከዘፋኞች ቴልማ ሆፕኪንዝ እና ጆይስ ቪንሰንት-ዊልያምዝ ጋራ በ1970 እ.ኤ.አ. ሠራው።

በተለይ የታወቁት በ1973 እ.ኤ.አ. ስለ ቀረጹት ዘፈን «ታይ አ ዬሎው ሪበን ራውንድ ዘ ኦል ኦክ ትሪ» («በጥንታዊው በሉጥ ዛፍ ዙሪያ ቢጫ ጥብጣብ እሰሪ» ነበረ። የቬትናም ጦርነት ዘመቻ ከዚያ ትንሽ በፊት ተጨርሶ አሁን ሰላም እየሆነ፣ ለመላው ዓለም ተወዳጅ ዜማ ሆነ። ከዚህ ስኬት ተነስቶ ቡድኑም ከሰኔ ወር 1966 ዓም (1974 እ.ኤ.አ.) ጀምሮ የራሱን ቴሌቪዥን ትርዒት ነበረው፣ ይህም እስከ ታህሳስ ወር 1969 ዓም (1976 እ.ኤ.አ.) ይታይ ነበር።

ከዚያም በኋላ እስካሁን ድረስ ሦስቱ ዘፋኞች ከጊዜ ወደ ጊዜ ዘፈኖችን እንደገና ለማጫወት ተባብረዋል።