Jump to content

ቸኮላታ

ከውክፔዲያ
ቸኮላታ ከረሜላ

ቸኮላታካካዎ ዛፍ (Theobroma cacao) ዘሮች ውጥ (ካካው) የተሠራ ጣፋጭ ከረሜላ አይነት ነው። ብዙ ስኳር ሳይጨመር ግን የቸኮላታ ጻዕም መራራ ነው።

ቸኮላታ መጠጥ እና የካካዎ ዛፍ ከጥንት ጀምሮ በሜክሲኮ ታውቀዋል፤ ስያሜውም «ቸኮላታ» እና በአለሙ ልሳናት የተዛመዱት ቃላት ሁላቸው ከናዋትል ስም «ሾኮላትል» ደርሰዋል። የተቀደሠ መጠጥ እንደ ሆነ ይቆጥሩትም ነበር። ከ1520 ዓም በኋላ የካካው ዘር ወደ አውሮፓ ገብቶ፣ እዛም በጣም ተወደደ። ዛሬ በመላው አለም አብዛኛው ካካው በምዕራብ አፍሪካ ይመረታል።

ቸኮላታ ግን ለለማዳ እንስሶች በተለይም ለድመት፣ ለውሻ፣ ለከብት ጤና የሚጎዳ ወይም የሚገድል መርዝ ነው።