ቸኮሌት ጄነዋስ ኬክ (1 ኪሎ ግራም ለማዘጋጀት)

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አዘገጃጀት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ዕንቁላሉንና ስኳሩን ጎድጎድ ያለ ዕቃ ውስጥ አድርጎ የሞቀ ውሃ የተጣደበት ብረት ድስት ውስጥ በማድረግ በዕንቁላል መምቻ እጥፍ ያክል እስኪነሣ መምታት፤
  2. ጎድጎድ ያለውን ዕቃ ከብረት ድስት ውስጥ ማውጣት፤
  3. ዱቄቱን ቤኪንግ ፓውደሩንና የካካዎ ዱቄቱን ለብቻ መቀላቀል፤
  4. በተጓዳኝ የኬክ መጋገሪያ ትሪ ላይ ትንሽ ቅቤ ቀብቶ ትንሽ የፉርኖ ዱቄት ላዩ ላይ ከነሰነሱ በኋላ ትሪውን በማንቀሳቀስ በእጅ ሳይነኩ አዳርሶ ዱቄቱን ማራገፍ፤
  5. የቤኪንግ ፓውደሩንና ዱቄቱን ድብልቅ ቀስ በቀስ ላዩ ላይ በተን እያደረጉ በዝርግ ጭልፍ ወይም በእጅ ማዋሃድ፤
  6. ቅቤውን አቅልጦ በመጨመር ማዋሃድ፤
  7. የተዘጋጀው የኬክ መጋገሪያ ላይ ውሁዱን ገልብጦ የሞቀ ዳቦ መጋገሪያ ውስጥ ማብሰል ወይም ከ200ሴንቲ ግሬድ እስከ 220ሴንቲ ግሬድ ለ30 ደቂቃ ማቆየት፡፡

(በዚህ መልክ የተዘጋጀውን ኬክ ብቻውን መብላት የሚቻል ሲሆን፣ ለተለያዩ የኬክ ዓይነቶች ማዘጋጃነትም ይውላል)