Jump to content

ኃያል እንሽላሊት

ከውክፔዲያ
ከሁሉ ዝነኛ አስፈሪ የሆነው በምዕራብ አሜሪካ የኖረው «ንጉሥ አምባገነን እንሽላሊት» አሁን እንደሚታሠብ ትንንሽ ላባዎች ነበሩት።

ኃያል እንሽላሊት (Dinosauria /ዳይኖሳውር/) በጥንት በቅድመ-ታሪክ የጠፋ ተሳቢ እንስሳ ክፍለመደብ ነበረ። እነዚህ ታላላቅ እንሽላሊቶች ከዘሬው እንሽላሊቶች መጠን እጅግ ይበልጡ ነበር፤ ከዝሆንም ይልቅ ይበልጡ ነበር። በዘመናዊ ሳይንስ ግመት ከ240 ሚሊዮን እስከ 66 ሚሊዮን ዓመታት በፊት ይኖሩ ነበር። በዚያው ጊዜ ምንም ጡት አጥቢ እንስሳ ገና ሳይኖር እነዚህ ትልልቅ ተሳቢዎች የምድር ጌቶች እንደ ነበሩ ይታመናል። ባጠቃላይ በሁለት እግሮች ሄደው ደካም ክንዶች እንደነበሩዋቸው ይታወቃል።

በዘመናዊ ሳይንቲስቶች ግመት ደግሞ አዕዋፍ ከኃያል-እንስላሊት ወገን ተወለዱ፣ ሌሎቹም ኃያል-እንሽላሊቶች በጠፉበት ጊዜ ከነርሱ መሃል አዕዋፍ ብቻ ተረፉ ባዮች ናቸው። ብዙዎች ታላላቅ እንስላሊት ባለ ላባ ቆዳ እንደ ነበራቸው ባለፈው ክፍለዘመን ታውቋል። እነዚህ ላባዎች መጀመርያ ለሙቀትና ለውበት አገለገሉ እንጂ ታላላቆቹ እንሽላሊቶች በረራ አላወቁም። በጊዜ ላይ አንዳንድ ዝርዮች ክንፍ እንዳገኙ ይመስላል።

የ«ኃያል ጥፍር» (Deinonychus) አፅም

ሳይንቲስቶችም እንደሚሉ፣ ከአዕዋፍ በቀር ሌሎቹ ኃያል-እንሽላሊቶች በአንድ ጊዜ አለቁ፣ ይህ የሆነው ወይም በእሳተ ገሞራ ምክንያት፣ ወይም ከሰማይ ታላቅ በረቅ ወድቆ ብዙ ጢስና ደመና በመፍጠሩ እንደ ነበር ይታሥባል።