Jump to content

ኅዋ

ከውክፔዲያ
ህልቁ መሳፍርት ከዋክብት በውኑ ኅዋ ውስጥ ተንጣለው

ኅዋ ቁስ አካል ያለን ሁሉ ተንጣለን የምንኖርበት ማብቂያ የሌለው፣ መዳሰስም ሆነ መታየት የማይችል፣ ነገር ግን አቅጣጫና አቀማመጥ ያለው፣ ቁሶችንና ክንዋኔያቸውን አቃፊ፣ ባለ 3 ቅጥ ነገር ነው።

ምንም እንኳ የውኑን አለም ለመረዳት የኅዋን ጽንሰ ሓሳብ መረዳት አስፈላጊ ቢሆንም እራሱ ኅዋ እንደ ጽንሰ ሓሳብ ጥያቄ በፍልስፍና ተመራማሪወች ዘንድ የወደቀብ ጊዜ ላይ ነው ያለነው። የኅዋ ምንነት ባሁኑ ጊዜ በ3 ተፎካካሪ አስተሳሰቦች ውስጥ ይገኛል እነሱም

  • ኅዋ በራሱ እራሱን የቻለ ነገር ነው ብለው የሚያምኑ
  • ኅዋ ማለት በነገሮች ዝምድና/ግንኙነት ምክንያት የሚፈጠር ሥፍራ ነው ብለው የሚያምኑ
  • ኅዋ ማለት አዕምሮዓችን የፈጠረው ጽንሰ ሃስብ ነው ብለው በሚያምኑ የፍልስፍና ፈርጆች ተከፍሎ ይገኛል። የትኞቹ ትክክል ናቸው የትኞቹ ስህተት ናቸውን እስካሁን አውቆ የሚያስረዳ የለም።