ነሐሴ ፲፮

ከውክፔዲያ

ነሐሴ ፲፮ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፵፮ ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ዮሐንስ ፳ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስማርቆስ እና ሉቃስ ደግሞ ፲፱ ዕለታት ይቀራሉ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች በዛሬው ዕለት በየዓመቱ ነሐሴ ፩ ቀን የሚጀመረውን ጾመ ፍልሰታ የሚፈቱበት ቀን ነው።

ታሪካዊ ማስታወሻዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

፲፰፻፶፮ ዓ/ም በጦርነት የተማረኩ ሰዎችን መብት ስለማስጠበቅና ስለማክበር የተዘጋጀው የጋራ ድንጋጌ (የጀኒቫ ኮንቬንሽን) በአሥራ ሁለት መሥራች አገሮች ተፈረመ። የቀይ መስቀል ማኅበርም አብሮ ተመሠረተ።

፲፱፻፷፬ ዓ/ም የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ሸንጎ (እንግሊዝኛ፡ International Olympic Committee) ሮዴዚያን (አሁን ዚምባብዌ) በዘረኛነቷ ምክንያት አባልነቷን ሠረዘ።

ልደት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

፲፰፻፺፮ ዓ/ም በዘጠና ሦስት ዓመታቸው እስከሞቱ ድረስ ለሀያ ሰባት ዓመታት ቻይናን የመሩት ዶንግ ዢያው ፒንግ ተወለዱ።

ዕለተ ሞት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

፲፱፻፸ ዓ/ም የመጀመሪያው የኬንያ መሪ ፕሬዚደንት ጆሞ ኬንያታ በተወለዱ በ ሰማንያ ስድስት ዓመታቸው አረፉ።


ዋቢ ምንጮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]