ነፋሳዊ ኤሌክትሪክ ማመንጫ

ከውክፔዲያ
ነፋሳዊ ኤሌክትሪክ ማመንጫ -- ከአበይት 4 ክፍሎቹ ጋር

ንፋሳዊ ኤሌክትሪክ ማመንጫንፋስአቅም ወደ ኤሌክትሪክ አቅም የሚቀይር መሳሪያ ነው። ኤሌክትሪክ ማመንጫው አብዛኛውን ጊዜ ከ4 አበይት ክፍሎች ይዋቀራል። እኒህም #ዘዋሪ ላባ#ጄኔሬተር ቆጥ#መቆጣጠሪያ ስርዓት እና #የነፋሳዊ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ሰገነት ናቸው ። ዘዋሪው ላባ በንፋስ ጉልበት ሲሽከረክረ፣ እርሱ በተራው ዳይናሞውን (የመግነጢስ እና ጥቅልል መዳብ ሽቦ ስርዓት) በመዘወር ኤሌክትሪክ እንዲመነጭ ያደርጋል። የመቆጣጠሪያ ስርዓቱ፣ የሚመነጨው ኤሌክትሪክ እንዳፈለገ እንዳይለዋወጥ፣ በተወሰነ መጠን እንዲረጋ የሚያደርግ የኮምፒዩተር ስርዓት ነው።

ቀላል የነፋሳዊ ኤሌክትሪክ ማመንጫ አሰራር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የነፋስ ማመንጫ ላባዎች አሰራር ደረጃዎች

ዘዋሪ ላባ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የኤሌክትሪክ ማመንጫን ለመስራት መጀመሪያ ከዘዋሪ ላባው ይጀመራል። ዘዋሪ ላባውን ከፒቪሲ ቱቦ መስራት በጣም ቀላልና ርካሽ ነው። ፒሲቪ ላስቲክ አይነት የቦምቦ ውሃ ቱቦ ነው።

ደረጃ 1፡ መጀመሪያ ሬዲየሱ 7.5 ሴንቲ ሜትር የሆነ፣ ቁመቱ 60 ሴንቲ ሜትር የሆነ ቱቦ መግዛት። ከዚያ ይሄን ቱቦ፣ በቁመቱ ትይዩ ከአራት መቁረጥ። ይህንን በቀጥታ ማድረግ ስለማይቻል፣ መጀመሪያ ቱቦውን በሰፊ ወረቀት መጠቅለልና፣ ያንን ወረቀት ከአራት በማጠፍ እንደገና ቱቦውን በመጠቅለል፣ የት ቦታ ላይ ቱቦው ቢቆረጥ አራት እኩል ቦታ እንዲከፈል በቀላሉ ማወቅ ይቻላል።

ደረጃ 2፡ ከስዕሉ ላይ እንደሚታየው ከእያንዳንዳቸው ቁራጮች ኮርነር ላይ 5 ሳንቲሜትር በ5ሳንቲሜትር አራት ማዕዘን ማስመር። በዚህች አራት ማዕዘን ውስጠኛ ኮርነር ላይ ቀዳዳ መንደል (መብሳት)። ከዚያ አራት ማዕዘኗን ቆርጦ ማውጣት። ቀዳዳው የመነደሉ ምክንያት፣ አራት ማዕዘኑ ተቆርጦ ሲወጣ ሊስፋፋ የሚችል ቁርጠት በኮርነሩ ላይ እንዳይተው ነው።

ደረጃ3፡ በስዕሉ መሰረት አራት ላባዎች ከአራቱ ቁራጮች ተቆርጠው ይወጣሉ። በእያንዳንዱ ላባ እጀታ ላይ ሁለት ሁለት ቀዳዳዎች ይነደላሉ።

ደረጃ 4፡ ከአራቱ፣ ሦስቱ በክብ ብረት ላይ በብሎን ይታሰራሉ። አራተኛው ላባ፣ ግልጋሎት ላይ የዋሉት ላባዎች ጉዳት ሲደርስባቸው ለመቀየሪያነት ያገልገላል። አራቱንም ላባ በአንድ ላይ መጠቀም ዋጋ የለውም።

ጄኔሬተር ቆጥ ውጥን

ጄኔሬተር ቆጥ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የዘዋሪው ላባ ሲሽከረከር የሚፈጥረውን አቅም ወደ ኤሌክትሪክ አቅም ለመቀየር ጄኔሬተር ወይንም ዳይናሞ ያስፈልጋል። ጄኔረተሮች የሚሰሩት ከጥቅልል ሽቦ እና ከመግነጢስ ሲሆን ለኤሌክትሪክ ማመንጫ የሚያስፈልግን ያክል ጄኔሬተር በ እጅ ለመስራት ከባድ ነው። ስለሆነም ለነፋስ ኤሌክትሪክ ማመንጫ የሚሆን ጄኔሬተር ወይም ከሱቅ መገዛት አለበት ወይንም ከተጣለ መሮጫ ማሽን ውስጥ በማውጣት፤ ወይንም ደግሞ ከተጣለ መኪና ውስጥ ኦልተርኔተሩን በማውጣት ለዚህ ጥቅም ማዋል ይቻላል።

ጄኔሬተሩ ክተገኘ በኋላ ከግራ በኩል በሚታየው ስዕል መሰረት በጄኔረተር ቆጡ ላይ በሚገባ ማሰር ግድ ይላል። ከጄኔረተሩ በተቃራኒ የቆጡ ጅራት በስዕሉ በሚታየው መልክ ይሰካል። የጅራቱ ተግባር የጄኔረተሩን ቆጥ በነፋስ ኃይል በማዞር ጄኔረተሩ ላይ የሚሰካው ዘዋሪ ላባ ምንጊዜም ወደተሻለ የንፋስ አቅጣጫ እንዲዞር ማድረግ ነው። ከቆጡ ስር የሰገነት ዘንጉ ይታያል። ዘንጉ በቆጡ ስር በሚበጅ ቀዳዳ በምግባት ቆጡን ሲደግፍ በዚያው መጠን ደግሞ ቆጡ እንደልቡ እንዲሽከረከር ያደርጋል። ውስጡ ክፍት ስለሆነ ከጄኔሬተሩ የሚመጡት ሽቦዎች በውስጡ ያልፋሉ።

የነፋሳዊ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ሰገነት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሰገነቱ ከመሬት ውስጥ በሲሚንቶ ይቀበርና ከመሃሉ ደግሞ በቋሊማ (መወጠሪያ ገመዶች) እንደ ድንኳን በችካል ይገተራል። የሰገነቱ ርዝመት ሲጨምር የሚያገኘውም ነፋስ ከፍ እያለ ስለሚሄድ ቁመቱ ከፍ እንዲል ፍላጎት አለ።

መቆጣጠሪያ ስርዓት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በዚህ ማሽን የሚገኘው ኤለክትሪክ መጠን እንደ ነፋሱ ጉልበት ይወሰናል። ሆኖም ግን የኤሌክትሪክ እቃዎች የኤሌክትሪክ መጠን መቀያየርን አይወዱም፣ ስለሆነም የጄኔሬተሩ የሚመነጨው ኤሌክትሪክ ከቁጥጥር ውጭ እንዳይሆን መጠኑን መቆጣጠር ግድ ይላል። ለዚህ ተግባር ዳዮድ እና መሰል ኤሌክትሪክ አካላትን መጠቀም ይቻላል።

ተጨማሪ ንባቦች/ ቪዲዮዎች (እንግሊዝኛ)[ለማስተካከል | ኮድ አርም]