ኑኩአሎፋ

ከውክፔዲያ

ኑኩአሎፋ (Nuku'alofa) የቶንጋ ዋና ከተማ ነው።

የቶንጋ ቤተ መንግስት

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር (1998 ዓ.ም.) 22,400 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 21°09′ ደቡብ ኬክሮስ እና 17°14′ ምዕራብ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

ኑኩአሎፋ በ1787 ዓ.ም. በቱኢ ካኖኩፖሉ ሙሙኢ ለመኖሪያቸው ተመረጠ። ይሁንና የቤተ መንግሥት ግቢ በሙዓ ከተማ ስለ ቀረ ኑኩአሎፋ ዋና ከተማ እስከ 1837 ዓ.ም. ድረስ አልሆነም።