ናኒ
Appearance
ናኒ ወይም ናኔ በሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ ከኡሩክ ነገሥታት ቀጥሎ የሱመርን ላዕላይነት ለከተማው ለኡር ያዘው። ይህ የኡር 2ኛ ሥርወ መንግሥት መጀመርያ ንጉሥ ይባላል።
በዝርዝሩ ላይ ለ120 (ወይም እንደ ሌላ ቅጂ ለ54) ዓመታት ነገሠ፤ እነዚህ ቁጥሮች ግን ምንም ታማኝነት የላቸውም። እንደዚያ ረጅም ዘመን እንደ ነበረው አይመስልም። ከናኒ በፊት የነበረው የኡሩክ 2ኛው ሥርወ መንግሥት መጨረሻ ንጉሥ አርጋንዴአ ሲባል፣ የአርጋንዴአ ስም ከሌላ ቅርስ ወይም ምንጭ ፈጽሞ አልተገኘምና ምናልባት ላዕላይነቱን ያልገዛ የኡሩክ ከንቲባ ብቻ ይሆናል። መጨረሻው ከሥነ ቅርስ የታወቀው የኡሩክ 2ኛ ሥርወ መንግሥት ንጉስ ሉጋል-ኪኒሼ-ዱዱ ሲሆን ናኒ ላዕላይነቱን የያዘው ከእርሱ ይመስላል።
የናኒ ስም አለዚያ የሚታወቀው የቱማል ጽሑፍ በተባለው ሰነድ ውስጥ ይጠቀሳል። በዚህ በኩል ናኒ የኒፑር መቅደስ እንደ ጠገነ ሲለን፣ እንግዲህ የሱመርን ላዕላይነት በውነት እንደ ያዘ ይመስላል። ልጁ መስኪአጝ-ናና ተከተለው።
ቀዳሚው የኡሩክ ንጉሥ ሉጋል-ኪኒሼ-ዱዱ |
የሱመር (ኒፑር) አለቃ 2187-2182 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ መስኪአጝ-ናና |
ቀዳሚው ባሉሉ? |
የዑር ገዢ 2219-2182 ዓክልበ. ግድም |