Jump to content

ንዋይ ደበበ

ከውክፔዲያ
ነዋይ ደበበ‎

ንዋይ ደበበ (፲፱፻፶፫ ዓ.ም. ተወለደ) ኢትዮጵያዊ ዘፋኝ እና ሙዚቃ ደራሲ ነው።

የሕይወት ታሪክ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ንዋይ ደበበ በጋሞጎፋ ክፍለ ሀገር በገለብና ሀመርባኮ አውራጃ በሀመር ወረዳ በ፲፱፻፶፫ ዓ.ም. ተወለደ። በተወለደበት አካባቢ ትምህርቱን እስከ ፬ኛ ክፍል ከተማረ በኋላ በ፲፱፻፷፫ ዓ.ም. ወደ አሰላ በመሄድ እዚያው እየተማረ ሳለ በአስተማሪውና በት/ቤት ጓደኞቹ ዘንድ አድናቆትን እያገኘ መጣ። በኋላም ላይ ንዋይ በቤተሰቦቹ የሥራ ዝውውር ምክንያት ወደ ሲዳሞ ሄዶ አርባምንጭ ከነማና በወላይታ ሶዶ የቀበሌ ኪነት ውስጥ ድምፃዊ ሊሆን ችሏል። ከዚያም ወደ አዲስ አበባ በመሄድ በ፲፱፻፸፯ ዓ.ም. የመጀመሪያ ካሴቱን ለማሳተም ችሏል። ንዋይ ከድምፃዊነቱ በተጨማሪም የዘፈን ግጥሞችና የዜማዎች ደራሲ በመሆኑ አገራችን ካሏት ጥቂትና ልዩ ድምጻዊያን አንዱ ነው። ንዋይ ደበበ ከታዋቂ ዘፈኖቹ አንዱ «የጥቅምት አበባ» የተባለው ሲሆን ዜማውንና ግጥሙን የደረሰው ገና የ8ኛ ክፍል ተማሪ በነበረ ጊዜ እንደሆነ ይናገራል።

የሥራዎች ዝርዝር

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዜማዎች፦

  • የጥቅምት አበባ
  • ሳፍ ሳፍ
  • እሸት በላሁኝ
  • ውለታሽ አለብኝ
  • ወንዝ ያፈራሽ
  • ፀዳል ውቢቷ
  • አልዋሽም
  • አሜን


  • እሰይ እሰይ