ኖቪያል
Appearance
ኖቪያል (novial) በኦቶ የስፐርሰን በ1920 ዓ.ም. የተፈጠረ ሰው ሠራሽ ቋንቋ ነው። ቃላቱ በተለይ ከጀርመንኛና ከሮማንስ ቋንቋዎች የተመሠረተ ነው። የስፐርሰን በ1935 ዓ.ም. ሲሞቱ ሀሣቡ በሥራ እንዳይውል ተደረገ። በ1980ዎቹ ግን ከኢንተርኔት የተነሣ አዲስ ትኩረት ተሰጥቶታል። እንደ ኤስፔራንቶ ፈጣሪ ዛምንሆፍ ሳይሆኑ የዴንማርክ ዜጋ የሆኑ አቶ የስፐርሰን ባለሙያ የቋንቋ ሊቅ ነበር። በሌሎች ሠው ሠራሽ ቋንቋዎች የተገኘው ቅጥ የሌለው ዘዴ አልወደዱም። ስለዚህ በቋንቋ ጥናት መርሆች ላይ የተመሠረተ ቋንቋ ለመፍጠር ጣሩ።
- እኔ - ሜ
- እኛ - ኑስ
- አንተ / አንቺ - ቩ
- እናንተ - ቩስ
- እሱ - ሎ, ሌ
- እነሱ - ሎስ, ሌስ
- እሷ - ላ, ሌ
- እነሷ - ላስ, ሌስ
- እሱ - ሉ, ሉም (ነገር)
- እነሱ - ሉስ, ሉሜስ (ነገሮች)
- ሜ ኦብሰርቫ ቩ - እመለከትሃለሁ
- ቩ ኦብሰርቫ ሜ - ትመለከተኛለህ
አገናዛቢ -n, -en (ን, -ኤን) ለተውላጠ ስም በመጨመር ይመለከታል።
- ሌ ኤስ ሜን ሁንዴ - የኔ ውሻ ነው።
- ሌ ኤስ ሜን - የኔ ነው።
- ኑሴን - የኛ
- ቩን - ያንተ / ያንቺ
- ቩሴን - የናንተ
- ሎን - የሱ
- ሎሴን - የነሱ
ፕሮቴክቴ - መጠበቅ ሜ ፕሮቴክቴ - እጠብቃለሁ ሜ ዲድ ፕሮቴክቴ / ሜ ፕሮቴክቴድ - ጠበቅሁ ሜ ሃ ፕሮቴክቴ - ጠብቄያለሁ ሜ ሃድ ፕሮቴክቴ - ጠብቄ ነበር ሜ ሳል ፕሮቴክቴ - ወደፊት እጠብቃለሁ ሜ ሳል ሃ ፕሮቴክቴ - ወደፊት እጠብቅ ነበር ሜ ሳሌድ ፕሮቴክቴ - ልጠብቅ ነበር ሜ ቩድ ፕሮቴክቴ - እጠብቅ ነበር ሌት ኑስ ፕሮቴክቴ - እንጠብቅ ፕሮቴክቴ! - ጠብቅ! ሌት ሎ ፕሮቴክቴ! - ይጠብቅ! ፕሮቴክቴንት - ጠባቂ ፕሮተክቴት - የተጠበቀ
የጌታ ጸሎት:-
- Nusen Patro kel es in siele,
- mey vun nome bli sanktifika,
- mey vun regno veni,
- mey vun volio eventa sur tere kom in siele.
- Dona a nus disidi li omnidiali pane,
- e pardona a nus nusen ofensos
- kom anke nus pardona a nusen ofensantes,
- e non dukte nus en li tento
- ma fika nus liberi fro li malum.
- ኑሴን ፓትሮ ኬል ኤስ ኢን ሲዬሌ
- መይ ቩን ኖሜ ብሊ ሳንክቲፊካ
- መይ ቩን ሬግኖ ቬኒ
- መይ ቩን ቮልዮ ኤቬንታ ሱር ቴሬ ኮም ኢን ሲዬሌ
- ዶና አ ኑስ ዲሲዲ ሊ ኦምኒዲያሊ ፓኔ
- ኤ ፓርዶና አ ኑስ ኑሴን ኦፌንሶስ
- ኮም አንኬ ኑስ ፓርዶና አ ኑሴን ኦፌንሳንቴስ
- ኤ ኖን ዱክቴ ኑስ ኤን ሊ ቴንቶ
- ማ ፊካ ኑስ ሊቤሪ ፍሮ ሊ ማሉም
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |